SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ SBS Audio
-
- Noticias
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
-
"በሐረሪ ሕብረተሰብ ውስጥ 40 ያህል የአለላ ስፌት ዓይነቶች መኖራቸውን ጥናቶች ያመለከታሉ" ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም
ወ/ሮ ዉዳድ ሳሊም፤ የጤና ባለሙያና አንቂ፤ ስለ ሐረሪ ማኅበረሰብ የአለላ ስፌት ባሕላዊ ቅርስነትና የማንነት መገለጫነት አስመልክተው ይናገራሉ።
-
የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ በረሃብና ተላላፊ በሽታ እየተፈነች እንደሆነና ከፍ ያለ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያሻት አሳሰበ
የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት 'ሕወሓት ወረራ ፈፅሞብኛል' ሲል ለፀጥታ አካላት፣ ለነዋሪዎች፣ የፌዴራል መንግሥትና ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አስታወቀ፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፌዴራልና የአማራ ክልል መንግሥታት ጋር ግጭት ውስጥ አይደለሁም አለ
-
የኤልያስ ዋንጫ፤ "ኤልያስ አገራችን ካፈራቻቸው የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጣም ለየት ያለ ተጫዋች ነው" አቤል አስመላሽ
በአዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ "የኤልያስ ዋንጫ" በሚል ስያሜ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ የዘገበ ፊልም እሑድ ሚያዝያ 6 ከቀትር በኋላ በሜልበርን ከተማ ለሕዝብ ዕይታ ቀርቧል። ዝነኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና ክለብ ተጫዋቾች በሥፍራው ተገኝተው አድናቆታቸውን ገልጠዋል።
-
በሲድኒ የቤተክርስቲያን ውስጥ ጥቃትን ተከትሎ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የተቃዋሚ ቡድን መሪ የአንድነት ጥሪ አቀረቡ
ኬንያ - ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እየተባባሰ ነው በሚል አስባብ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን የኤሌክትሪክ ሽያጭ ስምምነት የመከለስ ዕሳቤ እንዳላት ፍንጭ ሰጠች።
-
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰፈነው የጎሣ ፖለቲካ ኃላፊነት ወሳጅ ማን ነው? የ1966ቱ ተራማጆች ወይስ የወቅቱ የማንነት ፖለቲካ አራማጆች?
የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ "ኢትዮጵያዊነት ሞቷል፤ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ተዳክሟል ሊባል የሚችል አይመስለኝም። ኢትዮጵያን በውስጣቸው ይዘው የሚኖሩ፤ ታማኝ ሆነው ያሉ አሉ። በጎሣ ፖለቲካ ሁሉም ተጎጂ ነው" ሲሉ፤ አቶ አበራ የማነአብ "ኢትዮጵያዊነት ገለል ተደርጎ የሕዝብ አንድነት እንዲሻክር፤ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ወደ ግጭትም እንዲሸጋገር መንግሥት አስተዋፅዖ አለው" በማለት ስለ ጎሣ ተኮር የማንነት ፖለቲካ አንስተው አተያይቸውን ያጋራሉ።
-
"የመኢሶን ትልቁ አስተዋፅዖ ለውጡ ሕዝባዊ ይዘት እንዲኖረው በመሬት፣ ሕዝባዊ ድርጅቶችና የብሔሮች መብቶች ዙሪያ የተቻለውን ሁሉ ማድረጉ ነው" አቶ አበራ የ
"የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴና አቶ አበራ የማነ አብ፤ በኢትዮጵያ አብዮታዊ እንቅስቃሴ ወቅት የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ፖለቲካዊ ሚና ነቅሰው ይናገራሉ።