12 min.

የመንታ እናት ፖለቲካ ‪!‬ Sost kilo

    • Fictie

የ መ ን ታ ፡ እ ና ት ፡ ፖ ለ ቲ ካ

[ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ]

ለማበጠር ጀምራው ከነበር ፀጉሯ ውስጥ እጇን ወትፋ "ዋ………ይ"ብላ ጮኸች ። እሪታዋ ርዝመቱ በመሃል ቅላፄዋ እስኪለዋወጥ ነበር ። ጩኸቷን ተከትሎ ቤቱ ውስጥ ፀውታ (*ፀጥታ + ክውታ) ሰፈነ ። የድንገት ጩኸቷ ከሷ በፊት ሲርገበገቡ የነበሩ ሁለት የመንትዬ እንጥሎችን አርግቧል ።

ሣራ ያለግዜ የመጣችባት ፅጌዋ(*ፔሬዷ) ምቾት ነስታት ድምፅ የሚባል ነገር መስማት አስጠልቷታል። አንዴ አግና በለቀቀችው ጩኸቷ ያሰፈነችውን ፀውታ ቶሎ ለመጠቀም አሰበች ።

ከጆንያ ላይ ሃባ ክር መዛ ልጆቿ የተጣሉበትን ፊኛ የኮመዲኖው ጠርዝ ላይ ቋጠረችው። ድምር ለቅሷቸው ሲያስጨንቃት ወላ ፊኛውን መደንቆል ዳድቷት ነበር ።… ጧ! አርጋ አፈንድታ - ሠላሟን ያገኘች እንደው - ግን መጮህን መረጠች ።

ፊኛው ላይ እንደማይደርሱ ያወቁት አልቃሻ ልጆቿ በድንገቴ ቃጠሎ ጩኸቷ ተደናግጠው ለአፍታም ቢሆን እንደማደብ አሉ ። ለቅሷቸውን እንደፍሬን ቀጥ ማድረግ አሳፍሯቸው ነው መሰል ተንፈሳፍሰው ባላዝኖት ዋጡት ።

ረጭታውና የቤቱ ሰላም የቆየው ግን ለግማሽ ደቂቃ ነበር ። በሰማያዊው ኮመዲኖ ተደብቃባ የነበረችው እጀ'ዱሽ አሻንጉሊት (ታቲ ነው የሚሏት) ላይ አይናቸው እስክታርፍ ። አሻንጉሊቷ የተደበቀችበት ምክንያት መሳይ ጓደኛዋ (ቲታ) ጠፍታ እሷንለሁለቱም ማካፈል ከባድ ስለነበር ነው ።

ልክ ታቲን እንዳዩ የለቅሷቸው መቀጣጠያ ሌላ ጋዝ ሆነች ። ( *ሰው አይገባውም እንጂ መንታ ማሳደግ አንድአይነት ልብስ ከማልበስ የዘለለ ፖለቲካ ነው ። ዲፕሎማሲ ሳይችሉ እንዴትም የመንታ እናት አይኮንም)

* * *

ዛሬ ፥ የመንትየዎቹ ኢዛና'ና ሣይዛና አራተኛ ዓመት የልደት በዓል ነው ። አራቱ ዓመታት ምኔ እንደንፋስ እንዳለፉ ጭራሽ አታውቅም ። የእያንዳንዷ ቀን ርዝመት ግን ማለቂያ አልነበረውም ። ሌት ተኝታ ካደረችበት እንቅልፍ ባይኗ ሳይዞር ያነጋችው ይበልጣል ።

እንዲህ ያማረ ድግስ በቤቷ ስታዘጋጅ የመጀመሪያዋ ነው ። ሳምንት ሙሉ ስታስብበት ከርማ እንደሚሆን ለማድረግ አንድ ለናቷ የቀረቻትን አምሳ ብር ፈነከተች።

ቅዳሜ ደርሶ ደሞዝ እስክትወስድ መቆያ ቤስቲን እንደሌላት እያወቀች ለልደታቸው የሚሆኑ ነገሮችን ገዛዝታ እጇ ላይ የቀራት አስራ ስድስት ብር ነው ። ሆኖም ከድግሱ ኋላ ስለሚመጡ ግጥ ቀናት ማሰብ ጭራሽ አትፈልግም ።

ቲታ (አሻንጉሊቷ) የቆሰቆሰችውን ለቅሶ ገላቸውን በማጠብ ሸውዳ ከሐይቅ የታጨደ ለምለም ገሣ ትጎዘጉዝ ገባች ። መብል ከመደርደሯ ቀድማም የልብስ ሳጥኑን በመጎተት እንደጠረጴዛ የቤቱ መሃል ላይ አኖረችው ። በዘይት የተሟሸ ድስት ውስጥ የዘራችውን ፈንዲሻ በክዳኑ እንዳፈነች አፈካች ። እምትሰራበት ዳቦ ቤት ያስጋገረችውን ኲንስንስ ህብስትም አማትባ ቆራረሰች። ( * ቄስ ቢጠፋ ወንድ … ወንድ ጠፋ ተብሎ ዳቦ ሣይቆረስ አይቀር

Top-podcasts in Fictie

De Vrouw met Duizend Gezichten
Lex Noteboom | A.W. Bruna Uitgevers
Staatsgeheim
Loek Hennipman en Harm Duco Schut
Kater
VBK Audiolab / Politie Niet Betreden
De Moker
NPO Luister / NTR
Uncanny Valley
DWM | Realm
Tower 4
Bloody FM