
399 episodes

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ SBS
-
- News
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
-
የፋይዘር ኮሮናቫይረስ ክትባት አውስትራሊያ ውስጥ ለክትባትነት እንዲውል ይሁንታ አገኘ
*** የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፖሊስ በነገው ዕለት ለተቃውሞ የተዘጋጁ ሠልፈኞች የኮሮናቫይረስ ገደቦችን ጥሰው ቢገኙ ቅጣት እንደሚያገኛቸው አስጠነቀቀ
-
የአውስትራሊያ ቀን ለኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን ምን ማለት ነው?
አውስትራሊያ ውስጥ በየዓመቱ በጃኑዋሪ 26 የአውስትራሊያ ቀን ይከበራል፡፡ ዕለቱ በነባር ዜጎች ዘንድ በ'ኃዘን' ቀንነት ታስቦ ይውላል፡፡ በፍልሰት መጥተው አገረ አውስትራሊያን ያቆሙቱ የመጀመሪያዎቹ መርከቦቻቸው መልሕቆቻቸውን የጣሉባትን ጃኑዋሪ 26, 1788 በማሰብ በአውስትራሊያ ቀንነት ሰይመው ያከብራሉ፤ ያስከብራሉ፡፡ ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን ዶ/ር ግርማ ሞላ፣ ዶ/ር ሰለሞን ዋስይሁን፣ ወ/ሮ ሰናይት መብርሃቱና ወ/ሮ ሃሊማ ያሲን ግለ አተያያቸውን ያንጸባርቃሉ፡፡
-
ከገሚስ በላይ አውስትራሊያውያን ወጣቶች የአውስትራሊያ ቀን ከጃኑዋሪ 26 እንዲቀየር ይሻሉ
*** ጉግል ለአውስትራሊያ ሚዲያ ተቋማት ክፍያ እንድፈጽም ግድ የምሰኝ ከሆነ ግልጋሎቴን ለአውስትራሊያውያን ከመስጠት እቆጠባለሁ እያለ ነው
-
125ኛው የአድዋ ድል ከጋምቤላ እስከ አድዋ
*** የዘንድሮው የአድዋ ድል በዓል “አድዋ የኅብረብሔራዊ አንድነት አርማ” በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ይውላል
-
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሜልበርን
ወ/ሮ ጤንነት ታየ፤ በቪክቶሪያ የቋንቋዎች ትምህርት - ፉትስክሬይ ቅርንጫፍ የአማርኛ ቋንቋ መምህርትና ወ/ሮ ዝናሽ ሉሉ በቪክቶሪያ የቋንቋዎች ትምህርት - ካሮላይን ስፕሪንግ የክሪክሳይድ ኮሌጅ የአማርኛ ቋንቋ መምህርት፤ አውስትራሊያ ለተወለዱ ልጆች የአማርኛ ቋንቋን የመማር ፋይዳዎችና በማስተማር ረገዱ ስላሉ ተግዳሮች ይናገራሉ፡፡
-
የነባር ዜጎች የዕውቅና ጥያቄ ምንድነው?
‘ድምፅ’፣ ‘ዕውቅና’፣ ‘ሉዓላዊነት’፣ እና ‘የቃል ኪዳን ውል’ የሚሉ ቃላት አውስትራሊያ ከነባር ዜጎች ጋር ሊኖራት ስለሚገባት ትስስሮሽ የተሻለ ብልሃት ለማፈላለግ በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ተደጋግመው የሚደመጡ ናቸው፡፡