Nicodemus Asgedom
-
- Religion & Spirituality
This podcast will contain religious and spiritual book readings, spiritual poem readings, bible discussions and mezmurs. ተከታታይ መጽሐፉ እናነባለን ዝማሬ እና ትምህርት ይቀርባል::
-
ለቃና ዘገሊላው ተአምራትህ ሰላም እላለሁ !
በሰማይ ሳትታጣ በምድር የተገኘኸው ፣ ሁሉን ቻይነትህን ሥጋዌህ ያልሻረው ፣
ተዋሕዶህ እንደ ቃና ውኃ መለወጥ የሌለው ፤ ምድሩን እንዳልጠላ የምድር ነዋሪ ሆነህ ፣ ሰውነትን
እንዳልመረር ሰው ሁነህ መጥተህ የረዳኸኝ ፣ ደስታው ቶሎ ኀዘን ሲሆንብኝ ከጉድ ያወጣኸኝ የቃና
ዘገሊላ እድምተኛ ኢየሱስ ሆይ ሰላም እልሃለሁ !! -
የሚወዱህ አሜን ይላሉ
ትዳር ለሌለው የቤቱ ራስ ፣ አቅም ሲደክም ምርኩዝ ፣ ሲመሽ መብራት ፣ ዓይን ሲከዳ መሪ አንተ ነህና የቀኑን ምስጋና ፣ የሰንበትን ዘለላ ላንተ እናቀርባለን ። የሚወዱህ ሁሉ አሜን ይላሉ ። አሜን ያለህም በአማን በረከት ይባረካል ። አሜን ።
-