13 episódios

ካላንድራስ የአማርኛ ፖድካስት (RADIO) ነው:: ቃሉም ደግሞ አማርኛ [ካለ አንድ ራስ] እንደማለት የሚኾን
ነጻ ሃሳቦችን የምናንሸራሽርበት የኢንተርኔት ራዲዮ ሲሆን ማህበረሰብ ፣ ባህል ፣ ህግ ፣ ሃይማኖት . . . የማንነካው አይነኬ ፣ የማንዳሠው ጓዳ ጎድጓዳ ፣ የማንፈነቅለው የሃሳብ ድንጋይ አይኖርም።

ከወደዳችሁት እያዳመጣችሁ ባላችሁበት መተግበሪያ ላይ Rate በመስጠት እና Review በመጻፍ ብታግዙኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው።

Hosted by: Miki MAC

KALANDRAS Kalandras

    • Sociedade e cultura

ካላንድራስ የአማርኛ ፖድካስት (RADIO) ነው:: ቃሉም ደግሞ አማርኛ [ካለ አንድ ራስ] እንደማለት የሚኾን
ነጻ ሃሳቦችን የምናንሸራሽርበት የኢንተርኔት ራዲዮ ሲሆን ማህበረሰብ ፣ ባህል ፣ ህግ ፣ ሃይማኖት . . . የማንነካው አይነኬ ፣ የማንዳሠው ጓዳ ጎድጓዳ ፣ የማንፈነቅለው የሃሳብ ድንጋይ አይኖርም።

ከወደዳችሁት እያዳመጣችሁ ባላችሁበት መተግበሪያ ላይ Rate በመስጠት እና Review በመጻፍ ብታግዙኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው።

Hosted by: Miki MAC

    Episode 12 : ቃልኪዳን ታደሰ - ክፍል 2

    Episode 12 : ቃልኪዳን ታደሰ - ክፍል 2

    ቃልኪዳን ታደሰ በሙያዋ አርኪቴክትና የኢንቴሪየር ዲዛይን ባለሙያ ስትሆን ከካላንድራስ ጋር በነበራት የመጀመሪያው ክፍል ቆይታችን በህይወት ዘመኗ ስለገጠሙዋት ሁነቶች፣ ስለ ህይወት ተሞክሮዋ እንዲሁም ስለቤተሰቦቿና ልጅነቷ እየተጨዋወትን ውብ ቆይታ አድርገናል። ከቃልኪዳን ጋር የነበረን ቆይታ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሲሆን ብዙ ረብ ያላቸው ቁም ነገሮችን ከዳሰስንበት ዘለግ ያለ ጭውውታችን ስለስራዋና ከስራዋ ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ያወጋንበት ሁለተኛው ክፍል እነሆ።

    ይህንን ክፍል አዳምጣችሁ ስታበቁ እንደተለመደው አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ብትልኩልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው። ካላንድራስን ከወደዳችሁት እና ሌሎች በርካቶች ቢሰሙት የሚበጅ ነው የምትሉ ከሆነ ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ወይም ሼር በማድረግ እንዲሁም እና spotify, Apple podcast, Google podcast, Teraki Appን ተጠቅማችሁ የምታዳምጡ ከሆነ RATE በማድረግ እና REVIEW በመጻፍ ልታግዙኝ ትችላላችሁ።

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/kalandras/message

    • 36 min
    Episode 11 : ቃልኪዳን ታደሰ - ክፍል 1

    Episode 11 : ቃልኪዳን ታደሰ - ክፍል 1

    ቃልኪዳን ታደሰ በሙያዋ አርኪቴክትና የኢንቴሪየር ዲዛይን ባለሙያ ስትሆን በህይወት ዘመኗ ስለገጠሙዋት ሁነቶች፣ ስለ ህይወት ተሞክሮዋ እንዲሁም ስለቤተሰቦቿና ልጅነቷ እየተጨዋወትን ውብ ቆይታ አድርገናል። ከቃልኪዳን ጋር የነበረን ቆይታ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሲሆን ብዙ ረብ ያላቸው ቁም ነገሮችን የዳሰስንበት ዘለግ ያለው ጭውውታችን የመጀመሪያውን በዚህ ክፍል ቀጣዩን ደግሞ በሚቀጥለው ክፍል ይዘንላችሁ የምንቀርብ ይሆናል።
    ይህንን ክፍል አዳምጣችሁ ስታበቁ እንደተለመደው አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ብትልኩልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው። ካላንድራስን ከወደዳችሁት እና ሌሎች በርካቶች ቢሰሙት የሚበጅ ነው የምትሉ ከሆነ ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ወይም ሼር በማድረግ እንዲሁም እና spotify, Apple podcast, Google podcast, Teraki Appን ተጠቅማችሁ የምታዳምጡ ከሆነ RATE በማድረግ እና REVIEW በመጻፍ ልታግዙኝ ትችላላችሁ።

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/kalandras/message

    • 27 min
    Episode 10 : የፍላጎት ተዋረድ እና የሰው ልጅ ባህርይ (ከሔኖክ ጋር)

    Episode 10 : የፍላጎት ተዋረድ እና የሰው ልጅ ባህርይ (ከሔኖክ ጋር)

    ይህ የዛሬው ክፍል የካላንድራስ ፖድካስት 10ኛው ክፍል ሲሆን የዚህ ሲዝን መጨረሻም በዚሁ የሚጠናቀቅ ይሆናል። በምእራፍ ሁለት ደግሞ እንደተለመደው ከሁሉም አይነት የሃሳብ ዘለላዎች የተጠጉ ጥሩ ጥሩ ክፍሎችን ይዤላችሁ በቅርቡ ተመልሼ እመጣለሁ። እስከዚያው ግን መቆያ ይሆናችሁ ዘንድ የዩትዩብ ቻናሌ Mikimac Views ላይ በመሄድ በአይነታቸው ትንሽ ለየት ያሉና አጫጭር ቆይታ ያላቸውን ቪዲዮዎቼን እንድትመለከቱ በተጨማሪም SUBSCRIBE በማድረግ እንደሁልጊዜውም የስራዬ አጋር እና አበርቺ እንድትሆኑ እጠይቃለሁ።   

    ወደዛሬው የካላንድራስ ክፍል ስንገባ ስለአሜሪካዊው የስነ ልቦና ባለሙያ Abraham Maslow (አብርሃም ማስሎው) Hierarchy of needs ስለተባለው ቲዮሪው እየተጨዋወትን ቆይታ የምናደርግ ይሆናል። በዚህ የካላንድራስ ክፍል ላይም እንደሁልጊዜው እንግዳ ይዤላችሁ መጥቻለሁ። እንግዳችን ሄኖክ ይባላል። 

    ኤርትራዊ ሲሆን በአሁን ወቅት ነዋሪነቱ በአሜሪካን ሃገር ነው። የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው በባዮ ኬሚስትሪ የትምህርት ዘርፍ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪውን ደግሞ በፋርማሲ ትምህርት አግኝቷል። ሄኖክ ከትምህርቱ ባሻገር በስነልቦና እና የሰው ልጅ ባህርይ ላይ የተመሰረቱ ጥናቶች እና ትምህርቶች ቀልቡን እንደሚስቡትና ስለነዚሁ ጉዳዮች ከሰዎች ጋር መወያየት ፣ መጽሃፍትን ማንበብና ፣ ሰርክ አዳዲስ ተያያሽነት ያላቸው ሃሳቦችን መፈለግና ማወቅ ዝንባሌው ነው። ታዲይ ለዛሬም በዚሁ ጉዳይ ላይ የማስሎውን Hierarchy of needs theory ዘርዘር ባለ መልኩ እያጫወተን የሚቆይ የካላንድራስ እንግዳችን ነው።

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/kalandras/message

    • 35 min
    Episode 9 : ሌላ ሰው - አዲስ መንገድ (Aida Abdella)

    Episode 9 : ሌላ ሰው - አዲስ መንገድ (Aida Abdella)

    የካላንድራስ ክፍል 9 እንግዳችን አይዳ አብደላ ነች። በመኖር ውስጥ ስለገጠማት አንድ ትልቅ የህይወት መልክ ቀያሪ ክስተት ታጫውተናለች። የአይዳ ታሪክ ለብዙዎቻችን አስተማሪ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም። በታሪኳ ውስጥ ስላለው ጭብጥ እና አንቂ ቁምነገር መናገር ታሪኩን እንዳያበላሸው በሚል ስጋት ብዙ ዝርዝር ውስጥ አልገባም። 

    ይህንን ክፍል አዳምጣችሁ ስታበቁ እንደተለመደው አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ብትልኩልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው። ካላንድራስን ከወደዳችሁት እና ሌሎች በርካቶች ቢሰሙት የሚበጅ ነው የምትሉ ከሆነ ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ወይም ሼር በማድረግ እንዲሁም እና spotify, Apple podcast, Google podcast, Teraki Appን ተጠቅማችሁ የምታዳምጡ ከሆነ RATE በማድረግ እና REVIEW በመጻፍ ልታግዙኝ ትችላላችሁ።

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/kalandras/message

    • 47 min
    Episode 8: ስንት አየሁ? 🤔 / Sintayehu

    Episode 8: ስንት አየሁ? 🤔 / Sintayehu

    በዚህ የካላንድራስ ክፍል ከኢትዮጵያ ኬንያ ከኬንያ ደግሞ እስከ አሜሪካን ሃገር ድረስ የዘለቀና በብዙ የህይወት መልክና ውጣ ውረዶች የተፈተነ ድንቅ የቤተሰብ ታሪክ እንዳሥሣለን። ስደት ፣ ጥንካሬ ፣ ፅናት ፣ በፈተናዎች ያልወደቀ የቤተሰብ ፍቅር ፣ እምነት ፣ ስኬት . . . ብዙ ብዙ ቁምነገሮችን እንማርበታለን ብዬ አስባለሁ። 

    እንደተለመደው ሃሳብና አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን Instagram እና Telegram ላይ ልትልኩልን ትችላላችሁ። 

    ይህን ፖድካስት ከወደዳችሁት የምትሰሙበት መተግበሪያ ላይ Rate ብታደርጉልን ምስጋናችን የላቀ ነው።

    For more info about Kalandras

    www.mikimac.org/kalandras

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/kalandras/message

    • 34 min
    EPISODE 7 : ኢትዮጵያዊነት / Being Ethiopian?

    EPISODE 7 : ኢትዮጵያዊነት / Being Ethiopian?

    ኢትዮጵያዊነት ማለት ምንድነው?

    የኢትዮጵያዊነት ፍቺ ወይም ትርጓሜ እንደያንዳንዳችን የህይወት ትርጓሜና ተሞክሮ የሚወሰን ነው። 

    አንድ መንገድ ላይ ሊስትሮ እየጠረገ ህይወቱን የሚመራ ልጅ፣ በወሲብ ንግድ የምትኖር አንድ የቡና ቤት ሴት ፣ ስልጣን ላይ ያለ የተመቸው ባለጊዜ ፣ የሃገሩን ዳር ድንበር ለማስከበር ድንበርና ተጋድሎ ላይ ያለ የሃገር ወታደር ፣ የሚጠጣው ውሃ ማግኘት ታላቅ የህይወት ፈተና የሆነበት አንድ አርብቶ አደር ፣ የዝናቡን መዘግየት እያሰበ የጎተራው ባዶነት የሚያስጨንቀው ምስኪን ገበሬ ፣ ለሃገሬ የሚጠቅም ሃሳብ አለኝ በማለቱ ከወህኒ የተጣለው ጋዜጠኝ ፣ የታክሲ የሚከፍለው ገንዘብ በማጣቱ በቀን ብዙ ኪሎ ሜትሮችን በእግሩ እየተጓዘ የሚያስተምረው መምህር ፣ መሪ ነኝ ብለው ገዢ የሆኑና ዘውዱን የጨበጡ እለት ቃላቸውን ቅርጥፍ አድርገው የበሉ ጥጋበኞች በፈጠሩት ጸብ ህይወቱ እየተመሰቃቀለ ያለ የአንድ አካባቢ ህዝብ . . . 

    እነዚህ ሁሉ እንደጉራማይሌነታቸው ኢትዮጵያዊነትን የሚረዱበት መንገድም ብዙዎቻችን እንግዳ ተቀባይ ፣ የሰው ዘር መገኛ ፣ ሃይማኖተኛ ፣ ወ.ዘ.ተ . . . ከምንለው በእጅጉ የተለየ ነው።

    የዚህ የፖድካስት ክፍል አላማም መስማማት ላይ እንድንደርስ ወይም ለቃሉ ፍቺ የሚሆን ሃሳብ ላይ ተስማምተን እንድንለያይ ሳይሆን እስከዛሬ ይዘን የመጣነውን እውነት እንድንሞግትና የውስጥ ጥያቄዎቻችንን አውጥተን እንድንወያይበት ታሳቢ በማድረግ የቀረበ ነው:: 

    ሃሳብ አስተያየታችሁን ላኩልን።

    Follow us on INSTAGRAM and TELEGRAM

    ---

    Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/kalandras/message

    • 33 min

Top podcasts em Sociedade e cultura

NerdCast
Jovem Nerd
Rádio Novelo Apresenta
Rádio Novelo
É nóia minha?
Camila Fremder
Bom dia, Obvious
Marcela Ceribelli
Rádio Escafandro
Tomás Chiaverini
Que História É Essa, Porchat?
GNT