በዶናልድ ትራምፕ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ኢትዮጵያን ጨምሮ 36 ሀገራትን የጉዞ ዕቀባ ከጣለባቸው ጎራ የማካተት ዕቅድ አለው ተባለ። በጋዛ ሠርጥ በእስራኤል እና በአሜሪካ ድጋፍ ምግብ በሚታደልበት ቦታ በተከፈተ ተኩስ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። እስራኤል እና ኢራን አንዳቸው በሌላቸው ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ጨመረ። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ በቡድን ሰባት ሀገራት ስብሰባ ላይ የእስራኤል እና የኢራንን ግጭት ለማቆም በአራት ጉዳዮች ላይ ከሥምምነት ይደረሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸው አስታወቁ። በሰሜናዊ ሕንድ ሔሊኮፕተር ተከስክሶ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ።