ዓለም ዜና ቀጥሎ በሚቀርበዉ ልዩ የአዲስ አመት ዝግጅታችን፤ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አዲስ ዓመትን አስመልክቶ የደረሱንን ዘገባዎች እናደምጣለን። በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ከአገር ቤት ርቀዉ የአዲሱን ዓመት እንዴት እያከበሩት ነዉ፤ ዘገባ ይኖረናል። --እነዚህን ዘገባዎቻችን በሙዚቃ እያዋዘን በፊስቡክ የቀጥታ ስርጭት የሚከታተሉንን የዶቼ ቬለ ቤተሰቦች አስተያየቶችን በቀጥታ ስርጭት እናስደምጣለን