SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

"ትዝታ ትናንትን በምልስት በማውሳት ዛሬ ላይ ሕይወት ዘርተን የምናቆየው ነው፤ ለፊልሜ መጠሪያ ያደረግኩትም ቃለ መልዕክቱ ለልብና ለነፍስ ስለሆነ ነው"አራ

የ"ትዝታ" ዘጋቢ ፊልም ዳይሬክተር አራማዝት ካላይጂያን፤ አርመንያውያን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዓለም ውስጥ ከሠልፈኛ ባንድ ምሥረታ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ቀማሪነትና የዘመናዊ ሙዚቃ ጉልህ የጥበብ አሻራዎቻቸውን ስለሚዘክረው ፊልማቸው ጭብጦች ያወጋሉ። አርመናውያን በአጼዎቹ ዮሐንስ አራተኛ፣ ዳግማዊ ምኒልክና ቀዳማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥታት ውስጥ ከአድዋ ጦርነት ጣሊያንን መመከቻ መሣሪያ አበርካችነት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ግንባታዎችና በሌሎችም ዘርፈ ብዙ መስኮች ያበረከቷቸውን ሁነኛ አስተዋፅዖዎች ያነሳሉ። ትዝታ ነሐሴ 25 /ኦገስት 31 በሜልበርን Lido Cinemas ለሕዝብ ይቀርባል።