SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

የዘጸአት የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ህብረት ያሰራውን ህንጻ ቤ/ክ በመጪው ቅዳሜ ሊያስመርቅ ነው

አቶ ዳንኤል አለማር ከዘጸአት የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ህብረት የህንጻ አሰሪ ሰብሳቢ ፤ በሜልበርን ከተማ በመጪው ቅድሚ የሚመረቀው የቤተክርስቲያን ህንጻ ፤ ህብረተሰቡ ከሌለው አቅሙ ቀንሦ ለትውልዱ እና ለመጪው ትውልድ ያሳነጸው ሲሆን ፡ በህንጻ አሰሪው ኮሚቴው ስም ምስጋናዪን አቀርባለሁ ብለዋል ። አያይዘውም በምርቃቱ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲገኙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።