Great Truths Podcast (Amharic)

ዶ/ር ቤንጃሚን ዲን

This is the Amharic version of the Great Truths Podcast.ይህ ፖድካስት የእግዚአብሔር ቃልን በተሻለ መንገድ ለመረዳት እና የመፅሐፍ ቅዱስን መልዕክት ዛሬ ለእኛ ምን እንደሆነ ለማወቅ ይረዳናል። ታላቅ እውነት (Great Truths) ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የሆኑ የወንጌል አማኝ መሪዎችን (መጋቢዎች፣ እረኞች፣ ቄሶች፣ ሰባኪዎች፣ እና ወንጌላውያኖችን) ለማገልገል የሚፈልግ፣ ደግሞም በአለማችን ያሉ 660 ሚሊዮን ወንጌል አማኝ ክርስትያኖችን ከፍተኛ ጥራት ባላቸው የሚዲያ አማራጮች መፅሐፍ ቅዱስን ለማስተማር የሚሻ ተቋም ነው። ለበለጠ መረጃ እና የእያንዳንዱን ምዕራፍ ሙሉ መፅሐፍ ከተጨማሪ ግብዐቶች ጋር ለማግኘት ድህረ ገፃችንን ይመልከቱ https://amharic.greattruthsglobal.org/ 

  1. EPISODE 5

    መላእክት #5 | መላእክት በምን ዓይነት መልክ ይገለጣሉ ወይም ይታያሉ?

    በተለምዶ መላእክት ለሰው ልጆች በሥጋ ዓይን የሚታዩ ፍጥረታት አይደሉም፡፡ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ መላእክት በወንዶች መልክ የሚገለጡ ፍጥረታት ናቸው (ዘፍ. 18፡2፤ቁ. 16፤፤ 19፡1-22 መሳፍ. 13፡3-21፤ እብ 13፡2)፡፡ ከመለኮታዊ ሥልጣናቸው የተነሳ አንዳንዴ መላእክት የሚያስፈሩ ናቸው፡፡ በተፈጥሮ ባህሪያቸው መላእክት በሚታይ መልኩ ሲገለጡ የሚያስፈራ ሳይሆን በልዩ የእግዚአብሄር ክብርና ግርማ የተሞሉ እና በሚያስደንቅ ሁኔታም የሚገለጡ ናቸው (ዘኁ. 22፡31፤ 2 ነገስት 6፡17፤ ዳን. 10፡4-9፤ ማቴ. 28፡3፤ ሉቃ. 2፡9 እና ራእይ 10፡1-3)፡፡ በጥቂቱ ሊያስደንቀን የሚሞክረው ነገር ቢኖር ዮሃንስ ሁለት ጊዜ የእግዚአብሄርን መልእክት ወደርሱ ያመጣውን መልኣክ ሊያመልከው ወይም ሊሰግድለት ሞክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን መልኣኩ ራሱ ይህንን ጉዳይ እንደተቃወመው እንመለከታለን (ራእይ 19፡10 እና 22፡8)[1]፡፡ ይህም ማለት መላእክት ለእግዚብአሄር የሚገባውን ክብር ለራሳቸው ለማድረግ እንደማይፈልጉ ነው፡፡

    17 min

About

This is the Amharic version of the Great Truths Podcast.ይህ ፖድካስት የእግዚአብሔር ቃልን በተሻለ መንገድ ለመረዳት እና የመፅሐፍ ቅዱስን መልዕክት ዛሬ ለእኛ ምን እንደሆነ ለማወቅ ይረዳናል። ታላቅ እውነት (Great Truths) ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የሆኑ የወንጌል አማኝ መሪዎችን (መጋቢዎች፣ እረኞች፣ ቄሶች፣ ሰባኪዎች፣ እና ወንጌላውያኖችን) ለማገልገል የሚፈልግ፣ ደግሞም በአለማችን ያሉ 660 ሚሊዮን ወንጌል አማኝ ክርስትያኖችን ከፍተኛ ጥራት ባላቸው የሚዲያ አማራጮች መፅሐፍ ቅዱስን ለማስተማር የሚሻ ተቋም ነው። ለበለጠ መረጃ እና የእያንዳንዱን ምዕራፍ ሙሉ መፅሐፍ ከተጨማሪ ግብዐቶች ጋር ለማግኘት ድህረ ገፃችንን ይመልከቱ https://amharic.greattruthsglobal.org/ 

You Might Also Like