ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia

Connect for Culture Africa

የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት በባህል እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኙ የባህላዊ እና የፈጠራ ኢንዱስትሪ (CCIs) ላይ ያተኮረ ተከታታይ ክፍሎች ያሉት ጥልቅ ውይይት የሚካሄድበት ፖድካስት ነው፡፡ ሃሳብን በሚኮረኩቱ የተለያዩ ክፍሎች ባለሞያዎችን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ከህዝብ/መንግስት ድጋፍ አንስቶ እስከ ስራ ፈጠራ፣ ሰላም ግንባታና እና ዲሞክራሲ ባህል በኅብረተሰብ ውስጥ ያለውን ሚና ይዳስሳል፡፡ በተሾመ ወንድሙ የሚዘጋጀው ይህ ፖድካስት ለቅስቀሳ እንዲሁም ወጣቶችን ለማብቃት መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ሁሉም ክፍሎች በአማርኛ የሚቀርቡ ሲሆን የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ይኖራቸዋል፡፡ የበለጠ ለማወቅ የሚከተለውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ https://cfcafrica.org The CfCA Ethiopia Podcast is a series of powerful conversations around culture and the cultural and creative industries (CCIs) in Ethiopia. Through thought-provoking episodes, we engage with experts and stakeholders to explore the value of culture in society—from public funding and job creation to peacebuilding and democracy. Hosted by Teshome Wondimu, the podcast also serves as a tool for advocacy and youth empowerment. All episodes are in Amharic with English subtitles. Tune in and explore more at https://cfcafrica.org

  1. JAN 26

    Institutionalizing the Arts: Policy, Heritage, and Ethiopia's Creative Economy

    ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 14 ሥርዓተ-ጥበብን መገንባት፦ ፖሊሲ፣ ቅርስና የኢትዮጵያ የፈጠራ ኢኮኖሚ እንግዳ፡ አቶ ሰርፀ ፍሬ ስብሐት | አዘጋጅ ተሾመ ወንድሙ በክፍል 14 ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት አዘጋጅ ተሾመ ወንድሙ የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ከአቶ ሰርፀ ፍሬ ስብሐት ጋር ጥልቅ ውይይት ያደርጋል፡ ይህ ክፍል የኢትዮጵያን የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ከባሕላዊና በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ከተመሠረተ አሠራር ወጥቶ፣ ወደ ተደራጀና በፖሊሲ ወደተደገፈ ኢንዱስትሪ ለመቀየር የሚያስፈልጉ መሠረታዊ መዋቅራዊ ለውጦችን ይቃኛል፡፡ አቶ ሰርፀ የወመዘክርን ፋይዳ፣ የፖሊሲ ክፍተቶችን እና የዲጂታል ዘመኑ በፈጠራው ዘርፍ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ በተመለከተ ተቋማዊ ራዕያቸውን ያጋራሉ፡፡ በውይይቱ ላይ የሚነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች፡ ወመዘክርን የኢኮኖሚ ሞተር ስለማድረግ፡ የታሪክና የቅርስ ማከማቻነትን ለፈጠራ ኢኮኖሚ ግብዓትነት የመጠቀም አቅም፡፡ ብሔራዊ የኪነ-ጥበብ ፖሊሲና የሮያሊቲ ሥርዓት፡ ዘርፉን በሕግና በመዋቅር ለመደገፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት፡፡ የባለቤትነት መብትና የሜታ-ዳታ (Metadata) ቀውስ፡ የፈጠራ ባለሙያዎች ከሥራቸው ተገቢውን ጥቅም እንዳያገኙ የሆኑ ተግዳሮቶች፡፡ ዲጂታል ኢትዮጵያና የኤአይ (AI) ተፅዕኖ፡ ቴክኖሎጂ ለፈጠራ ሥራዎች የያዘው ዕድልና በሰው ልጅ የፈጠራ ብቃት ላይ የደቀነው ስጋት፡፡ ከፈቃደኝነት ወደ ተቋማዊ አሠራር፡ ጥበብን በፖሊሲ የተደገፈና በጠንካራ መሠረት ላይ የቆመ ኢንዱስትሪ የማድረግ አስፈላጊነት፡፡ ይህ ክፍል ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ለታሪክና ቅርስ ተመራማሪዎች፣ ለፖሊሲ አውጪዎች፣እንዲሁም የኢትዮጵያን የፈጠራ ኢኮኖሚ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሸጋገር ፍላጎት ላላቸው ሁሉ የቀረበ ልዩ ውይይት ነው፡፡ ይመልከቱ፣ ያድምጡ እንዲሁም ውይይቱን ይቀላቀሉ፡፡ በባህል፣ በፖሊሲ እና በአፍሪካ የፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ የሚያጠነጥኑ ተጨማሪ ውይይቶችን ለመከታተል ሰብስክራይብ ያድርጉ፡፡ Title: Institutionalizing the Arts: Policy, Heritage, and Ethiopia's Creative Economy Connect for Culture Africa Ethiopia Podcast Episode 14 Guest: Sertse Fre Sibhat | Host: Teshome Wondimu In Episode 14 of the Connect for Culture Africa Ethiopia Podcast, host Teshome Wondimu sits down with Sertse Fre Sibhat, Director General of the National Archives and Library of Ethiopia (Wemezekir). This episode explores the fundamental structural changes required to transition Ethiopia's arts sector from traditional and volunteer based practices into an organized, policy backed industry. Sertse shares his institutional vision regarding the significance of Wemezekir, existing policy gaps, and the impact of the digital era on the creative sector. Key topics include: Archives as creative economy engines: Transforming heritage into a resource for national development. Policy roadmaps and royalty frameworks: Building the structural backbone of the arts sector. Solving the intellectual property metadata crisis: Addressing the technical and legal gaps in creators rights. Navigating Digital 2030 and AI risks: The impact of emerging technology on human creativity and cultural integrity. From Volunteerism to Institutions: Moving beyond "passion-led" work to a structured, policy driven economic sector. This episode is essential viewing for cultural practitioners, heritage researchers, policymakers, and anyone dedicated to the institutionalization of Ethiopia's vast creative and historical wealth. Watch, listen, and join the conversation. Subscribe for more conversations on culture, policy, and creative industries in Africa.

    1h 26m
  2. Thread of Identity: Fashion as Culture and Industry

    JAN 2

    Thread of Identity: Fashion as Culture and Industry

    ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 13 የማንነት ክሮች - ፋሽን እንደ ባህል እና እንደ ኢንዱስትሪ እንግዳ፡ ማኅሌት ተክለ/ማርያም | አዘጋጅ ተሾመ ወንድሙ   በክፍል 13 ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት ፤ አዝጋጅ ተሾመ ወንድሙ የሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ መስራች እና አዘጋጅ ከሆነችው ማኅሌት ተክለ/ማርያም ጋር ውይይት ያደርጋል፡፡   ይህ ክፍል የኢትዮጵያን ፋሽን እና የፈጠራ ኢንዱስትሪ እድገት፣ተግዳሮቶችን እና መፃኢ እጣ ፈንታን ይቃኛል፡፡ ማኅሌት ከውጭ አገራት እስከ አገር ውስጥ የዘለቀ ጉዞዋን፣ በአፍሪካ ውስጥ እስከ አሁን ድረስ የዘለቀ የፋሽን መድረክን ስለመገንባቷ በተጨማሪም ስለማንነት፣ባህል እና ለፋሽን ኢንዱስትሪው ስላሉ እድሎች በውይይቱ ላይ ታጋራለች፡፡ በውይይቱ ላይ የሚነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች • ፋሽን እንደ የባህል እና የእለት ተእለት መገለጫ በኢትዮጵያ  • የኢትዮጵያ እና አፍሪካ ፋሽን ኢንዱስትሪዎች እድገት • ዲዛይነሮች የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች፡ የማምረት ሂደት፣ቁሳቁሶች፣ፖሊሲ፣ በብዛት ማምረት • ፋሽን ዊክ ለፋሽን የመሟገቻ፣ለቱሪስት መስኅብነት እና ለስራ ፈጠራ መድረክ ሆኖ የማገልገል አቅሙ • "በኢትዮጵያ የመተረተ'' ፤ ሰዎች በአገራቸው ምርት እንዲኮሩ ማድረግ • ዘላቂነት፣ ለአካባቢ የሚስማማ፣ ለህዝብ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ የሚሸጥ እንዲሁም ባህልን የሚያከብር ፋሽን • በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ የፋሽን ገበያዎች የኢትዮጵያ ስፍራ ይህ ክፍል በፈጠራ ስራ ላይ ለተሰማሩ፣ለፖሊሲ አውጪዎች፣ለስራ ፈጣሪዎች፣ለተማሪዎች እንዲሁም በአፍሪካ በባህል ላይ ለተመሰረተ እድገት በሙሉ ፍላጎት ያላቸው ሁሉ ሊመለከቱት የሚገባ ነው፡፡  ይመልከቱ፣ያድምጡ እንዲሁም ውይይቱን ይቀላቀሉ፡፡ በባህል፣በፖሊሲ እና በአፍሪካ የፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ የሚያጠነጥኑ ተጨማሪ ውይይቶችን ለመከታተል ሰብስክራይብ ያድርጉ፡፡   Title: Thread of Identity: Fashion as Culture and Industry Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast | Episode 13   Guest: Mahlet T/Mariam | Host: Teshome Wondimu   In Episode 13 of Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast, host Teshome Wondimu sits down with Mahlet Teklemariam (Mahlet T/Mariam), founder and organizer of Hub of Africa Fashion Week, Addis Ababa. This episode explores the growth, challenges, and future of Ethiopia's fashion and creative industries. Mahlet shares her journey from the Ethiopian diaspora to building one of Africa's most consistent fashion platforms, and discusses fashion as identity, culture, industry, and opportunity. Key topics include: • Fashion as cultural identity and everyday life in Ethiopia • The growth of Ethiopian and African fashion industries • Challenges designers face: production, materials, policy, and scale • Fashion weeks as platforms for advocacy, tourism, and job creation • "Made in Ethiopia" and building pride in local products • Sustainability, ethical fashion, and environmental responsibility • Ethiopia's place in African and global fashion markets This episode is a must-watch for creatives, policymakers, entrepreneurs, students, and anyone interested in culture-led development in Africa. Watch, listen, and join the conversation. Subscribe for more conversations on culture, policy, and creative industries in Africa.

    57 min
  3. 12/12/2025

    The Canvas Speaks: Visual and Fine Arts in Ethiopia

    ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት፤ ክፍል 12 ''ሸራ ይናገራል፤ የእይታ ጥበባት እና ሥነ-ጥበብ በኢትዮጵያ'' እንግዳ፡ የእይታ ጥበባት አርቲስት፣ ገጣሚ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ፕሮፌሰር፤ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን   በዚህ አነቃቂና አይን ከፋች ክፍል፣ የኢትዮጵያን የእይታ ሥነ-ጥበባት እና የሥነ-ሥዕል ጥበብ ዘርፍ ጥልቀታቸውን፣ታሪካቸውን እና ተግዳሮታቸውን እንዳስሳለን፡፡ እንግዳችን ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን በሥነ-ጥበብ እና በሙዚየም ስራ ውስጥ ለበርካታ አስርት ዓመታት እንደ የፈጠራ ሰራተኛ፣መምህር እና መሪ በመሆን ያገለገሉበትን ልምድ ይዘው የቀረቡ ሲሆን በጋራ በመሆን የሚከተሉትን ጉዳዮች እንወያያለን፡፡ ·         በኢትዮጵያ የባህል ሥነ-ምህዳር ወስጥ የጎደለውን መሰረተ ልማት ·         ሙዚየሞች ለምን ከማከማቻ ስፍራነት ባለፈ ማደግ እንዳለበቸው ·         የመሰነድ፣የትችት እና የምርምር ጠቃሚነት ·         ማኅበረሰቦች ኪነ-ጥበባዊን ችሎታ እንዴት ተንከባክበው ማሳደግ እንደሚችሉ ·         የመንግስት ፖሊሲ፣ኢንቨስትመንት እና አህጉራዊ ትስስሮች ሚና ·         ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ የፈጠራ ትስስሮችን እንዴት እንደምትገነባ ሰብስክራይብ በማድረግ ወደ ፊት የሚወጡ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ክፍሎችን ይከታተሉ፡፡ ከታች ኮሜንት በማድረግ ውይይቱን ይቀላቀሉ! Connect for Culture Africa Ethiopia Podcast– Episode 12 🎨 The Canvas Speaks: Visual and Fine Arts in Ethiopia Guest: Bekele Mekonnen – Visual Artist, Poet, and Professor at AAU Ale School of Fine Arts and Design In this inspiring and eye-opening episode, we explore the depth, history, challenges, and untapped opportunities of Ethiopia's visual and fine arts sector. Our guest, Bekele Mekonnen, brings decades of experience as a creator, educator, and leader in fine arts and museum practice. Together we discuss: The missing infrastructure within Ethiopia's cultural ecosystem Why museums must evolve beyond storage spaces The importance of documentation, critique, and research How communities can nurture artistic talent The role of government policy, investment, and continental networks How Ethiopia can rebuild its creative connections within Africa Subscribe & stay updated on future episodes of Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast. Comment below and join the conversation! #1percentforculture #sustainablepublicfunding #EthiopianArt #FineArts #VisualArts

    1h 5m
  4. Stages of Change: The Transformative Power of Theatre

    11/21/2025

    Stages of Change: The Transformative Power of Theatre

    ክፍል 11፡ የለውጥ መድረኮች: የትያትር ኃይል ለዘላቂ ለውጥ እንግዳ፡ መዓዛ ወርቁ፤ ጸሐፊ ተውኔት አቅራቢ፡ ተሾመ ወንድሙ   በዚህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ከዝነኛዋ ጸሐፊ ተውኔት መዓዛ ወርቁ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የባህል ተረክ ውስጥ ትያትር የተጫወተውንና እየተጫወተ ያለውን ከፍተኛ ሚና እንዳስሳለን፡፡   በትምህርት ቤቶች እና ሆቴሎች ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፤ሀገርን ለአንድ ዓላማ እስከማስተባበር ድረስ፣መዓዛ የኢትዮጵያ ትያትር አስደማሚ ጉዞን ታስቃኘናለች፡፡ በተጨማሪም ትያትር ለፊልም፣ቴሌቪዥን፣ትምህርት፣የሀገር ግንባታ ያለውን አስተዋጽኦ እንዲሁም የጋራ ማንነትን በመቅረጽ ረገድ ያለውን አስተዋጽኦ ጸሐፊ ወደ ኋላ በመመለስ ትዳስሳለች፡፡    በዚህ ክፍል የሚከተሉትን እናነሳለን • የኢትዮጵያ ትያትር ጥልቅ ታሪክ • ትያትር በኢትዮጵያ ፊልም እና ቴሌቪዥን ላይ የሚሳተፉ ባለተሰጥኦዎችን እንዴት ኮትኩቶ እንዳሳደገ • ኪነ-ጥበብ ለህብረተሰብ እድገት እና ውይይት ለምን አስፈላጊ እንደሆነ • የፖሊሲ፣የገንዘብ ድጋፍ እና ውይይት ከፍተኛ አስፈላጊነት • የትያትር መጻኢ እጣ ፈንታ በኢትዮጵያ እና አፍሪካ   ይህ ለአርቲስቶች፣ፖሊሲ አውጪዎች፣ተማሪዎች እንዲሁም በባህል የለውጥ ኃይል ለሚያምኑ ሁሉ ጥልቀት ያለው ምልከታን የሚሰጥ እንዲሁም ወቅታዊ ውይይት ነው፡፡   በኢትዮጵያ የፈጠራ እና የባህላዊ ኢንዱስትሪ ላይ ተጨማሪ ውይይቶችን ለመከታተል ሰብስክራይብ ያድርጉን እንዲሁም አዲስ ክፍሎች እንዳያመልጥዎት የደወል ምልክቱን ይጫኑ!     Episode 11: "Stages of Change: The Transformative Power of Theatre" Guest: Meaza Worku (Playwright) Host: Teshome Wondimu   In this episode of the Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast, we sit down with acclaimed playwright Meaza Worku to explore the powerful role theatre has played—and continues to play—in Ethiopia's cultural narrative.   From its early beginnings in schools and hotels to its role in national mobilization, Meaza takes us through the remarkable journey of Ethiopian theatre. She reflects on its contribution to film, TV, education, nation-building, and the shaping of collective identity.   We discuss: • The deep-rooted history of Ethiopian theatre • How theatre cultivated Ethiopia's film and TV talent • Why art is essential for societal growth and dialogue • The crucial need for policy, funding, and private-sector support • The future of theatre in Ethiopia and Africa   This is an insightful and timely conversation for artists, policymakers, students, and anyone who believes in the transformative power of culture.   Subscribe for more conversations on Ethiopia's creative and cultural industries. Don't forget to turn on notifications so you don't miss upcoming episodes!   #1percentforculture #sustainablepublicfunding #ConnectForCultureAfrica #Theatre #CreativeIndustry

    57 min
  5. Learning the Arts: The Role of Education in Cultural Development

    10/31/2025

    Learning the Arts: The Role of Education in Cultural Development

    ጥበብና ትምህርት፡ በባህል ልማት ውስጥ የትምህርት ሚና |ክፍል 10| ወደ ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት 10ኛ ክፍል እንኩዋን በደህና መጣችሁ! በዚህ ክፍል የሰላምና ሙዚቃዊ መስራች እና ዋና ዳይሬክተር ተሾመ ወንድሙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ምክትል ዲን/ኪዩሬተር፣ አርቲስት እንዲሁም ተመራማሪ ከሆኑት አገኘሁ አዳነ  ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ በመቅረጽ ረገድ የሥነ-ጥበብ ትምህርት ያለውን ሚና ይዳስሳሉ፡፡ የሚዳሰሱ ርዕሶች ·         የሥነ-ጥበብ ትምህርት ከስር መሰረት የመሰጠቱ ጥቅም ·         ለኢትዮጵያ ሥነ-ጥበብ የነበሩ ታሪካዊ እና ዘመናዊ አስተዋጽኦዎች ·        የሥነ-ጥበብ ስራዎችን ጠብቆ በማቆየት እና ሞያን በማሳደግ ረገድ ያሉ ተግዳሮቶች ·         ለአርቲስቶች፣ትምህርት ቤቶች እና ማኅበረሰቦች ያሉ እድሎች ይህ ክፍል ትምህርት እና ባህል በጋራ በመሆን እንዴት ብሩህ እና የሰለጠነ ህብረተሰብን እንደሚቀርጹ ለአርቲስቶች፣መምህራኖች እንዲሁም የባህል ወዳጆች እጅግ ጠቃሚ ምልከታን ይሰጣል፡፡ ይህን ክፍል () እንዲሁም () ላይ በአማርኛ ማድመጥ ይችላሉ፡፡ Welcome to Episode 10 of Connect for Culture Africa Ethiopia! In this episode, Teshome Wondimu sits down with Agegnehu Adane, Vice Dean at Addis Ababa University's Alle School of Fine Arts and Design, to explore the critical role of arts education in shaping Ethiopian society. Topics discussed include: The importance of grassroots arts education Historical and modern contributions to Ethiopian arts Challenges in archiving and professional development Opportunities for artists, schools, and communities Whether you're an artist, educator, or cultural enthusiast, this episode offers invaluable insights into how education and culture intersect to shape a vibrant, civilized society. #1percentforculture #sustainablepublicfunding #ArtsEducation #FineArts #ConnectForCulture

    1h 18m
  6. Owning Creativity: The State of Copyright and IPR in Ethiopia

    10/10/2025

    Owning Creativity: The State of Copyright and IPR in Ethiopia

    ክፍል 9፡ የፈጠራ ባለቤትነት፡ የቅጂ እና የአእምሯዊ ንብረት መብት በኢትዮጵያ| ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ይህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት በኢትዮጵያ የፈጠራ ዘርፍ ውስጥ እጅግ አንገብጋቢ የሆኑትን የቅጂ መብት እና የአእምሯዊ ንብረት መብትን በጥልቀት ይዳስሳል፡፡ የሚዳሰሱ ጉዳዮች   ·         አሁን በሚገኙ ህጎች እና ረቂቅ ፖሊሲዎች መካከል ያለው ክፍተት ·         የበርን ኮንቬንሽን እና ዓለም አቀፍ ፕሮቶኮሎች ጥቅም ·         የጋራ አስተዳደር ማኅበራት ሚና ·         ኢትዮጵያ ለምን አሁን ወደ ተግባር መግባት እንዳለባት ·         በዘርፉ የገንዘብ ድጋፍ፣ትምህርት እና ትብብር ጥቅም ይህን የባለሞያን ምልከታ የያዘውን ክፍል የፈጠራ ባለሞያዎች፣ፖሊሲ አውጪዎች፣ የባህል መሪዎች እና የአፍሪካ ባህል ተሟጋቾች ሊያዩት የሚገባ ነው፡፡ ላይክ እና ሰብስክራይብ ማድረግ አይርሱ! This episode of Connect for Culture Africa Ethiopia Podcast dives into one of the most urgent issues in Ethiopia's creative sector: Copyright and Intellectual Property Rights. We explore: The gaps in current laws and draft policies The significance of the Berne Convention and international IP protocols The role of collective management societies Why Ethiopia needs to act now—not later The importance of funding, education, and unity in the sector Featuring expert insights from the sector's professional, this episode is a must-watch for creators, policy makers, cultural leaders, and advocates for African arts. Don't forget to like, share, and subscribe! #1percentforculture #sustainablepublicfunding #CreativeEconomy #BerneConvention #ConnectForCultureAfrica Youtube-link: https://youtu.be/4BL9xTqRskw

    1h 3m
  7. Beyond the Spotlight: Circus as a Tool for Empowerment| Teklu Ashagir | CfCA - Ethiopia #8

    09/19/2025

    Beyond the Spotlight: Circus as a Tool for Empowerment| Teklu Ashagir | CfCA - Ethiopia #8

    ከመድረክ ባሻገር፡ ሰርከስ እንደ አስቻይ የጥበብ ዘርፍ| ተክሉ አሻግር ከተሾመ ወንድሙ ጋር| ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ሰላም ኢትዮጵያ ከኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ እንቅስቃሴ ጋር በጋራ ወደ ሚያቀርበው ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት እንኳን በደህና መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍል ተሾመ ወንድሙ ከኢትዮጵያ ሰርከስ ብሔራዊ ማኅበር ፕሬዝደንት ከተክሉ አሻግር ጋር በመሆን ሰርከስ ያለምንም ተቋማዊ ድጋፍ ወይም መሰረተ-ልማት እንዴት ህይወትን እንደለወጠ፣ወጣቶችን እንዳበቃ እንዲሁም ኢትዮጵያ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ያላትን ዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ እያደረገ እንደሚገኝ አይን ገላጭ ውይይት ያካሂዳሉ፡፡ የሚዳሰሱ ርዕሶች ·         ኢትዮጵያ በሰርከስ ጥበብ ከዓለም አቀፍ መሪዎች መካከል የመሆኗ ሁኔታ ·         ከስር ጀምሮ እስከ ብቁ ባለሞያነት ድረስ ያለ ጉዞ ·         ሰርከስ እንደ ለውጥ እና ዲፕሎማሲ መሳሪያ ·         የሰርከስ ኢኮኖሚያዊ አንድምታ ይህ ውይይት ለፖሊሲ አውጪዎች፣ የፈጠራ ስራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች እንዲሁም ለህዝብ፤ የፈጠራ ኢንዱስትሪዎች ሀገራትን በመለወጥ ረገድ ያላቸውን ኃይል እንዲገነዘቡ ጥሪ የሚያቀርብ ነው፡፡ ይመልከቱ እንዲሁም ኃሳብዎን ከስር ያጋሩ! ስለኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ እና 1% የብሔራዊ በጀትን ለባህል ስለማዋል እንቅስቃሴ ለመረዳት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ፡ https://cfcafrica.org/ ይህን ክፍል በስፖቲፋይ (Spotify) እና አፕል ፖድካስት (Apple podcast) ማድመጥ ይችላሉ፡፡

    59 min
  8. Writing Our Truths: The State of Literature in Ethiopia

    08/29/2025

    Writing Our Truths: The State of Literature in Ethiopia

    የሀገር ገፆች፡ የስነ-ጽሁፍ ሁኔታ በኢትዮጵያ ክፍል 7 - ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት ደራሲ የዝና ወርቁ እና ተሾመ ወንድሙ በጋራ በመሆን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ  ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችንና እድሎችን ይዳስሳሉ፡፡ የንባብ ልምድ ከማዳበር እስከ ፖሊሲ አስተዋጽኦ፣የህትመት ችግሮች፣ የቋንቋ ብዝኃነት እና ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን በመግለጽ ረገድ የዘርፉ መፃኢ እጣ ፈንታ በዚህ ውይይት ይነሳሉ፡፡ የሚካተቱ ርዕሶች ዝርዝር ጸሀፊዎች በኅብረተሰብ ውስጥ ያላቸው ሚና በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ውስጥ የኢትዮጵያ የስነ-ጽሁፍ ሁኔታ ለጸሀፊዎች የመሰረተ-ልማት እና ድጋፍ ያለበት ሁኔታ ንባብን እንዲሁም መጻፍን ለማበረታታት መደረግ ስላለባቸው የማበረታቻ ስራዎች  ትምህርት፣ጥልቅ ስሜት እና ተሰጥኦ ያላቸው ግንኙነት ባህልን በመጽሐፍት አማካይነት ለትውልድ ማስተላለፍ እንዲሁም ፖሊሲ እና ህትመት ያለበት ሁኔታ ይመልከቱ፣ያጋሩ እንዲሁም የውይይቱ አካል ይሁኑ! ተጨማሪ የባህል፣ፈጠራ እና ማኅበረሰብ ላይ የተዘጋጁ የፖድካስት ይዘቶች እንዲደርስዎ ላይክ፣ኮሜንት እና ሰብስክራይብ ያድርጉ፡፡ Writing Our Truths: The State of Literature in Ethiopia Episode 7 – CfCA Ethiopia Podcast Featuring: Writer Yezina Worku with Teshome Wondimu In this powerful episode, we sit down with renowned Ethiopian writer Yezina Worku to explore the challenges and opportunities in the world of Ethiopian literature today. From cultivating a reading culture to the role of policy, publishing struggles, language diversity, and the future of storytelling in Ethiopia — this conversation dives deep into what it means to write our truths and build a literary future. Topics include: The writer's role in society The state of literature in different Ethiopian languages The lack of infrastructure and support for writers Efforts that need to be carried out to promote reading and writing The intersection of education, passion, and talent preservation of culture through books, the status of publishing and policy  Watch, share, and be part of the conversation. Don't forget to like, comment, and subscribe for more content on culture, creativity, and community. #1percentforculture #sustainablepublicfunding

    1h 7m

About

የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት በባህል እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኙ የባህላዊ እና የፈጠራ ኢንዱስትሪ (CCIs) ላይ ያተኮረ ተከታታይ ክፍሎች ያሉት ጥልቅ ውይይት የሚካሄድበት ፖድካስት ነው፡፡ ሃሳብን በሚኮረኩቱ የተለያዩ ክፍሎች ባለሞያዎችን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ከህዝብ/መንግስት ድጋፍ አንስቶ እስከ ስራ ፈጠራ፣ ሰላም ግንባታና እና ዲሞክራሲ ባህል በኅብረተሰብ ውስጥ ያለውን ሚና ይዳስሳል፡፡ በተሾመ ወንድሙ የሚዘጋጀው ይህ ፖድካስት ለቅስቀሳ እንዲሁም ወጣቶችን ለማብቃት መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ሁሉም ክፍሎች በአማርኛ የሚቀርቡ ሲሆን የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ይኖራቸዋል፡፡ የበለጠ ለማወቅ የሚከተለውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ https://cfcafrica.org The CfCA Ethiopia Podcast is a series of powerful conversations around culture and the cultural and creative industries (CCIs) in Ethiopia. Through thought-provoking episodes, we engage with experts and stakeholders to explore the value of culture in society—from public funding and job creation to peacebuilding and democracy. Hosted by Teshome Wondimu, the podcast also serves as a tool for advocacy and youth empowerment. All episodes are in Amharic with English subtitles. Tune in and explore more at https://cfcafrica.org