Drum of Changes

Zelalem Demissie

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power. Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of transformation resonating across the continent.

  1. 6d ago

    ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት፦ የሩሲያ አፍሪካ ግንኙነት ለፍትሐዊ የዓለም ስርዓት

    “ባለብዙ ዋልታ የዓለም ስረዓት መፈጠር በተለይም ለአፍሪካ አማራጭ የሌው ጉዳይ ነው [...] ሩሲያም ይህንን ነገር ይዛ መቅረቧ አስፈላጊ ነው [...] ሰርጌ ላቭሮቭ ያንሱት እና ስለአፍሪካ ሁለንተናዊ ነፃነት የሚያወሳው ‘የአፍሪካ ዳግም መነቃቃት’ አፍሪካውያን የምንቀበለው ሲሆን፣ ሩሲያ ፍትሃዊ የዓለም ስረዓት እንዲፈጠር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው” ሲሉ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አስራት ኤርሞሎ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ በቀዳሚነት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 7 እስከ 10 ቀን 2026 በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ያደረጉትን ከፍተኛ ደረጃ ጉብኝቶ መነሻ አድርገን የይፋዊ የሥራ ጉብኝቶቹን ስትራቴጂካዊ አንድምታዎች እንቃኛለን። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ሐሳባቸዉን የሚያጋሩን በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር መምህር፣ ተማራማሪ ዶ/ር አስራት ኤርሞሎ ናቸው። በተከታዩ ጉዳያችን ደግሞ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 15 ቀን 2026 የጀመረዉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ሂደት በተመለከተ ከብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) ጋር የተደረገን አጠር ያለ ቆይታ ይዞላችሁ ይቀርባል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  2. Jul 11

    የአፍሪካና ሩሲያ የጋራ ህልም፤ ወደ ባለብዙ ወገን ዓለምአቀፋዊ ሥርዓት

    የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላፍሮቭ ከሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 3 1ቀን 2018 ዓ.ም በአፍሪካ ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በቡሩንዲ አጠናቅቀዋል፡፡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የሰርጌላቭሮቭን ይፋዊ የስራ ብዙ የአፍሪካ አገራት የዩኒፖላር ሥርዓትን ለመግታት ወደ ሩሲያ እንደሚመለከቱ ተናግረዋል።  “በምዕራባውያን የበላይነት የሚመራው የዩኒፖላር (የአንድ ወገን) ሥርዓትና መዋቅራዊ ማስተካከያ ፕሮግራሞች (ስትራክቸራል አድጀስትመንት ፕሮግራምስ) በአፍሪካና በተቀረው ዓለም ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድረዋል” ሲሉ በላይ በየነ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ መምህር በላይ በየነን አነጋግረናል። በዚሁ ዝግጅት ሁለተኛው ክፍል በሶሻሊስት የአውሮጳ ሀገራት ውስጥ ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ኢትዮጵያውያንን አበርክቷቸውን ለመዳሰስ ከቀድሞ የሶሻሊስት ሀገር ተማሪና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ሰለሞን አሊ (ዶ/ር) ጋር ሰፊ ዉይይት አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  3. Jul 11

    የመጨረሻው ምሽግ፦ በአገር በቀል ዘሮችና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ የተጋረጠው አደጋ በአፍሪካ

    “በምዕራባውያን አምሳል የተነደፉ የግብርና ምርምር ተቋማት፣ የአገር በቀል የእህል ዘሮቻችን አዋጭነትን ዝቅ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ አለባቸው። ነገር ግን እውነታው ዘሮቻችንን ያጣን ዕለት ማንነታችንን የማጣታችን ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት እነዚህ የውጭ ኃይሎችና ግዙፍ ኩባንያዎች ሁሉንም ነገር ተቆጣጥረውታል። በአፍሪካ እስካሁን እጃቸውን ያላስገቡበት ብቸኛው ዘርፍ ቢኖር ምግባችንና የምግብ ስርዓታችን ብቻ ነበር። አሁን አሁን ይሄንኑ የመጨረሻ ምሽጋችንን ለመቆጣጠር በከፍተኛ ፍጥነት እየመጡ ነው” ሲሉ ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሩቅ ባሉ ኃይሎች መካከል የሚቀሰቀሱ ግጭቶች እንደምን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን የዕለት ጉርስ ላይ ስጋት እንደሚሆን እንመረምራለን፤ ይህ ሁኔታም የምግብ ዋስትና በሎም ዋነኛ የብሔራዊ ደህንነት እና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የመሆኑንም ነገር ያስቃኘናል። ለዚህም የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት ዋና አስተባባሪ የሆኑትን ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  4. Jul 8

    የላቭሮቭ ይፋዊ የስራ ጉብኝት፡ ኢትዮጵያ ፣ ብሪክስ እና ባለብዙ ዋልታው ዓለም

    "ሩሲያ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ መልካም ወዳጅ ሆና ለዘመናት ቆይታለች። በተቃራኑው ደግሞ የምእራቡ አለም፣ አፍሪካን በማሳነስ በምእራቡ ላይ ጥገኛ ሆና እንድትቀር እየሰራ ይገኛል [...] ሩሲያ ግን የአፈሪካን ራስን የመቻል ፍላጎት በመሰረታዊነት የተረዳች ሀገር ነች" ሲሉ የሕግ ባለሞያ እና የዓለም ማቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ ብሩክ መላኩ ለስፑትኒክ ካፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ላቭሮቭን የኢትዮጵያ ጉብኝት አንስተን ሁለንተናዊ አንድምታዎቹን እንቃኛለን። ለዚህም የሕግ ባለሞያ እና የዓለም ማቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ ብሩክ መላኩን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጉዳያችን  በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ ያደረግን ሲሆን፣ የቅኝ ግዛት ውርስ የሆነው የ"ሉዓላዊነት" እሳቤ በአፍሪካ ያመጣቸውን መዘዞች እንቃኛለን።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  5. Jun 15

    የተዘረፉ ቅርሶች፡ የአፍሪካን የታሪክ እውነት ለማስመለስ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ትግል

    “[…] ከአፍሪካ በጉልበት የተወሰዱ የተለያዩ ቅርሶች ለአፍሪካውያን ባለቤቶቻቸው ሳይመለሱ በአውሮፓ ሙዚየሞች እንዲቆዩ የሚደረገው ደህንነታቸው በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ ነው የሚለው መከራከሪያ እውነታነት የለውም። ምክንያቱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሙዚየሞች በጦር መሳሪያውች ተደብድበዋልና። በቅርቡ በፈረንሳዩ ሉቭር ሙዚየም ጭምር በርካታ ስርቆቶች ተፈጽመዋል። ስለዚህ በምዕራቡ አገራት ያሉ ሙዚየሞች በሙሉ አስተማማኝ ናቸው ማለት አይቻልም” ሲሉ የማህበራዊ ጉዳዮች ተመራማሪው አሉላ ፓንከረስት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚ ጉዳዩ፣ የአፍሪካን የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ትክክለኛ መኖሪያቸው ለመመለስ የሚደረገውን ታሪካዊ፣ ስልታዊ እና ጥልቅ ስሜት የሚንጸባረቅበትን አፍሪካዊ እንቅስቃሴ ያስቃኘናል። ለዚህም የማህበራዊ ጉዳዮች ተመራማሪውን አሉላ ፓንከረስት (ዶ/ር) አነጋግረናል። እ.ኤ.አ. ሰኔ 12 እና 12 ቀን 2026 በአዲስ አበባ የተካሄደው አንደኛው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ እና የቴክኖሎጂ ውድድር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የምንቃኝበት ሁለታኛው ጉዳያችን ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ ሐሳባቸዉን ሊያጋሩን ብሩክ ከድር (ዶ/ር)፣ አናንድ አንባላጋን እና ፋራይ ቺዳሩን አነጋግረናል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  6. Jun 4

    ሴንት ፒተርስበርግ ዓለምዓቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም፣ ለአፍሪካ ምን አማራጮችን ይዞ መጥቷል?

    "አፍሪካ ከዚህ ጉባኤ [ከ ሴንት ፒተርስበርግ ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክ ፎረም] ትጠቀማለች [...] አሜሪካ በኢራን፣ በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት ላይ የጣለቻቸው ማዕቀቦ ምዕራባውያኑ በፋይናንስ አስተዳደር ረገድ እምነት የሚጣልባቸው አጋሮች ሊሆኑ እንደማይችሉ እያሳየ ጉዳይ ነው። በዚህም ምክንያት ሀገራት የዕዳ ቀውስን ለመፍታት ጨምሮ ለራሳቸው የሚበጀ የተሻለ ጎዳናነ መሻት ይኖርባቸዋል [...] ጉባኤው ከዚህ አንፃር ፋየዳው የጎላ ነው" ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ቀዳሚው ጉዳይ እ.ኤ.አ. ከ ሰኔ 3 እስከ 6 በሩሲያዋ ሴንት ፒተርስበርግ እየተካሄደ ባለው ሴንት ፒተርስበርግ ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክ ፎረም 2026 ላይ ያተኩራል፡፡ ''ለአፍሪካስ ምን አማራጮችን ይዞ ይመጣል?'' ስንል እንጠይቃለን። በጉዳዩ ላይ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያውን ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁልተኛው ጉዳያችን ደግሞ የታንዛንያ ፕሬዝደንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን የሩሲያ ጉብኝት አንድምታዎች በስፋት እንዳሰሳለን። ለዚህም ታንዛንያውያን የምጣኔ ሀብት እና የዓለም አቅፍ ፖለቲካ ተንታኞችን አነጋገርናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  7. May 25

    የአፍሪካ ቀን እና የአንድነቱ መሐንዲሶች፡ የታሪክ አሻራ እና የዲፕሎማሲ ጉዞ

    “የአፍሪካውያን ማንነታችንን የምናከብርበት ብቸኛው ቀን ይህ [የአፍሪካ ነፃነት ቀን] በአህጉር ደረጃ ሊከበር የሚገባው ይመስለኛል። ትርጉሙን አባቴ [ከተማ የፍሩ] ያደረገውን፣ ኳሜ ንክሩማህ እና አፄ ኃይለ ሥላሴ ያከናወኑትን ማስታወስ ይኖርብናል” ሲሉ መኮንን ከተማ ይፍሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በየዓመቱ ግንቦት 17 ወይም እ.ኤ.አ ግንቦት 25 የጋራ ጉዟችንን እና ቅርሳችንን ለማክበር በመላው አፍሪካ የሚታሰበው ታሪካዊው የአፍሪካ ቀን ሆኖ ይከበራል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ በጥልቅ ተከፋፍላ የነበረችውን አፍሪካ በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ስር ያሰባሰበውን ስትራቴጂካዊ ጥበብ ለመረዳት በአህጉሪቱ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያለውን ያንን ወሳኝ ወቅት መለስ ብለን እንቃኛለን። ለዚህ የእውቁ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ልጅ እንዲሁም ጸሐፊ የሆኑትን መኮንን ከተማ ይፍሩን ጋብዘናል። በሁለትኛው ጉዳያችን ደግሞ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሳሰረ በመጣው ዓለም ውስጥ የአፍሪካን ባህል፣ ማንነት እና የታሪክ ባለቤትነትን የመጠበቅ ወሳኝ የትግል አውድን እንመለከታለን።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  8. May 21

    የአፍሪካ ቀን፦ በትውስታ፣ በትርጉሙ እና ባልተጠናቀቀው የአንድነት ጉዞ መካከል

    የአፍሪካ ቀን የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ ሚያዝያ 25፤ 1963 የተመሰረተበትን ቀን የሚዘክር እለት ነው፤ በየዓመቱም ይከበራል። “የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ወቅት የነበረው የአንድነት መንፈስ በዛሬዪቱ ተቀዛቅዟል [...] የአፍሪካ ነፃነት ቀንም የፍሪካን ነፃነት እያከበርን፣ ስለአፍሪካ እጣፈንታ ኮስተር ብለን የምንወያይበት እለትም ሆኖ ማለፍ ነው ያለበት”ሲሉ የአፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዋና ዳይሬከተር አሮን ስይፉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ፣ የነፃዪቱ አፍሪካ ተላሚዎች፣ አባቶች ያለሟትን አፍሪካ ዛሬ ካለችበት ሆነን እንቃኛታለን። አሮን ሰይፉ፣ የአፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዋና ዳይሬከተር በመረጥነው ርእስ ዙሪያ ሀሳባቸውን አጋርተውናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

About

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power. Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of transformation resonating across the continent.