Leakeberhan Podcast

פרק 29- ריאיון פודקאסט עם גב' הייווט זוודו עקרת בית ואם לשניים בוגרים, תושבת קריית ביאליק

ወ/ሮ ህይወት ዘውዱ ይባላሉ ። የሁለት ጎረምሳ ልጆች እናት ናቸው።

አባታቸው አቶ ዘውዱ ሠለሞን ፣ እናታቸው ደግሞ ወ/ሮ ሣሃሌ ያዕቆብ [ነፍሳቸውን ይማር] ይባላሉ ።

የአባታቸው ወላጆች ሠለሞን ዳዊት እና አበበሽ ዮናስ [ነፍሳቸውን ይማር] የሚባሉ ሲሆን የእናታቸው

ወላጆች ደግሞ

ሊቀ ካህናት ያዕቆብ ይሥሐቅ እና ማሚት ዓናንያ [ነፍሳቸውን ይማር] ይባላሉ።

አባታቸው የተወለዱት ጨጭሆ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሲሆን፣ እናታቸው ደግሞ ስሬል ሊባኖስ በተባለው ቦታ ነው የተወለዱት ።

ወ/ሮ ህይወት በስሜን አካባቢ ልዩ ጎጡ ሹሃዳ በተባለው ቦታ ገና ህፃን እያሉ የለቀቁት ሲሆን ፀገዴ ነበር ያደጉት።

ወደ ፀገዴ የሄዱበት ምክንያትም እሚታቸው ሊቀ ካህናት የፀገዴ ሃይማኖት መሪ እንዲሆኑ ተጠይቀው ወደዚህ ቦታ በመሄዳቸው ምክንያት ነው።

በዚህ ቦታ ሊቀ ካህኑ

ለ17 ዓመታት ያህል የሃይማኖት መሪ ሁነው አገልግለዋል።

የአልጋ ቁራኛ የነበሩት እሚታቸው ያኔ የልጅነት ጉልበት ስለነበራቸው አሰቸጋሪ የሆነውን መንገድ እያዘሉና በበቅሎ እየጫኑ በ1976 እ.ኢ.አ የ 5 ቀን መንገድ ጉዞ ተጉዘዋል ።

የፀገዴ መንገድ አስቸጋሪ እና መኪና የማይገባበት ቦታ በመሆኑ ምክንያት ወደ ወገራ ለመድረስ 12 ጊዜ ወንዙን ተሻግረዋል ።

እዚያም ለ 6 ዓመት በሃይባ ቆይተዉ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ተጓዙ ፣ ወደ እስራኤል ሃገር ለመግባትም 8 ወር ያህል እየተጠባበቁ ቆይተዋል።

አዲስ አበባ እንደገቡ

በ8 ኛው ወር የካህኑ የእሚታው ወንድም ሮቤል ይሥሐቅ [ነ.ይ] ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ።

ቀጥሎም እሚታቸው ሊቀ ካህን ያዕቆብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

እሚታቸው በሞቱ ከ 3 ሳምንት በኋላ ልጃቸው ቤተሰብ ያዕቆብ [ነ.ይ] በመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ።

በአንድ ወር ውስጥ 3 ነፍስ ቀብረዋል። ይህን ሁሉ ችግር ተቋቁመው እተመኘዋት አገር እስራኤል ከገቡ በኋላ"እስራኤል" የተባለዉ ልጅ ወልደው ልያቅፉና በልጃቸው ስነ ምግባርና ተግባር እጅግ ደስተኛ መሆናቸው ለፖድካስት ለኣከብርሃን ገልጸዋል ።

הגב' היווט זוודו, עקרת בית, אמא לשני בוגרים, תושבת קריית ביאליק,

הינה אישה אמיצה וגיבורה, על אף המכשולים הרבים בדרכה התמודדה

בגבורה והגיעה לישראל שאליה השתוקקה שנים רבות.