ከሆስፒታል ዉጪ ለመውለድ ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ፤ ለምን? ከህይወቴ ታደሰ ጋር (MPH)

እናትHood | EnatHood

በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ ታደሰ ጋር ስለ ሶስተኛ ልጇ የወሊድ ዝግጅት ፣ ለምን ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ተጉዛ ከሚድዋይፍ ጋር ለመውለድ እንዳቀደች ፣ የእናትነት ጉዞዋን እና ለሎችም ተያያዥ ነገሮችን ተጨዋውተናል። በጣም ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች። ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን። ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት። ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። እንደ እቅድዋና ምኞትዋ ሶስተኛ ልጇን በ ማዋለጃ ማዕከል (Birthing Center) ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ወልዳለች። እንኳን ደስ አለሽ እያልን በተከታታይ ስላካፈለችው ልምድ እናመሰግናታለን። ህይወቴ በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በIG & YT ⁠ ታካፍላለች። በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ሶስት ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት።

Pour écouter des épisodes au contenu explicite, connectez‑vous.

Recevez les dernières actualités sur cette émission

Connectez‑vous ou inscrivez‑vous pour suivre des émissions, enregistrer des épisodes et recevoir les dernières actualités.

Choisissez un pays ou une région

Afrique, Moyen‑Orient et Inde

Asie‑Pacifique

Europe

Amérique latine et Caraïbes

États‑Unis et Canada