የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ፣ነጻ ጋዜጠኞችን ማዋከብን እንዲያቆሙ ተጠየቁ። ሂዩመን ራይትስ ዋች ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፣ሀሳባቸውንና አመለካከታቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው የታሰሩትን በሙሉም በአስቸኳይ እንዲለቁ ጥሪ አቅርቧል። ባሕር ዳር ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የመኪና አደጋ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ 11 ሰዎች ሞቱ ። 10 ሰዎችም ቆሰሉ ለፍልስጤም መንግስት እውቅና የሚሰጡ ሀገራት ቁጥር እየጨመረ ነው። ዛሬ ኒውዮርክ በሚካሄድ ጉባኤ ተጨማሪ ሀገራት ለፍልስጤም መንግሥት እውቅና ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።