የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪዎች ከሶስት ሳምንት በፊት ያሰሯቸዉ ሁለት የሸገር ኤፍ ኤም ጋዜጠኞች ዛሬ በዋስ ተለቀቁ።ጋዜጠኞቹ እንዲለቀቁ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎችና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ተቋማት ሲጠይቁ ነበር።-ለጋዛ ሕዝብ ርዳታ ጭነዉ የነበሩ ጀልባዎችን የእስራኤል ጦር በሰዉ አልባ አዉሮፕላን ደብድቧል መባሉ እንዲጣራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠየቀ---።የእስራኤል ጦር ዛሬ ጋዛ ዉስጥ 40 ሰዎችን ገድሏል።---የሩሲያና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሐገራት ጠብና ፍጥጫ እየከረረ ነዉ።ትንሺቱ የቀድሞ የሶቭየት ሕብረት ሪፐብሊክ ኢስቶኒያ ከሩሲያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር እያጠረች ነዉ።