Drum of Changes

Zelalem Demissie

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power. Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of transformation resonating across the continent.

  1. 3d ago

    ከኔቶ ባሻገር፡ ደህንነት፣ ሉዓላዊነት እና አፍሪካ እየተለወጠ ባለው ዓለም ውስጥ ያላት ቦታ

    አሜሪካን ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የኢንዶ-ፓስፊክ ስትራቴጂ ኔቶን ወደ አዲስ የውድድር አውድ እንዲገባ እያደረገው ይገኛል። ይህ ደግሞ መረጋጋትን ሳይሆን አዲስ ቅራኔን ብቻ ነው የሚጋብዘው። “አሁን እኮ የኔቶ ዓላማ የጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ መፍጠሪያ እና ማሰፋፊያ ወደ መሆን አዘንብሏል [...] የአፍሪካ ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው በኢኮኖሚ ነፃነት እና በራሷ የንግድ ማዕቀፎች እንጂ ከውጭ በሚመጡ ውሱን እርዳታዎች ብቻ አይደለም […] እኛ አፍሪካውያን የምንፈልገው አካታች የዓለም ሥርዓትን እንጂ አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት ውጥረት አይደለም” በማለት በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ መምህር እንዳለ ንጉሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ኔቶ ወደ እስያ-ፓስፊክ የሚያደርገው ስትራቴጂካዊ መስፋፋት ከብሪክስ እያደገ ከመጣው ባለብዙ ዋልታ አስተሳሰብ ጋር እንዴት እንደሚጣጣም በዋናነት ይዳስሳል። መምህር እና ተመራማሪ እንዳለ ንጉሴ በዚህ ጉዳይ ላይ ወቅታዊ ማብራሪያ የሚሰጡን ዕንግዳችን ናቸው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  2. Sep 2

    የሳህል ህብረት ስልታዊ የሉዓላዊነት እንቅስቃሴ፦ የቀጠናዊ ኃይልን ትርጉም እንደገና መበየን

    “ካፒታሊዝም [የምዕራቡ] በመሰረታዊነት የተመሰረተው በኢኮኖሚ ብዝበዛ ላይ ነው [...] አሁን የቀድሞ የፈረንሳዪ ቅኝ ግዛቶች «የቅኝ ግዛት መገበያያን» አንጠቀምም ባሉ ጊዜ የነዚህ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች እስከ ፖለቲካዊ ግድያዎች ድረስ ገጥሟቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ «የቅኝ ግዛት መገበያያዎች» ለአውሮፓውያኑ የአመት ገቢያቸው ነው፣ የአፍሪካን ገበያ የሚቆጣጠሩበት ነው” ሲሉ እንዳለ ንጉሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት ወደ ቀጠናዊ ሉዓላዊነት ቁርጠኛ ሽግግር እያደረገ ወደሚገኘው የሳህል ቀጠና ይወስደናል። ለዚህም በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑትን እንደለ ንጉሴ አውርተናል። ድረም ኦቭ ቼንጅስ በሁለተኛው ጉዳዩ፣ የሀገርበቀል የሰላም ጥረቶች ተምሳሌት የሆነው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር መድረክ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካዊ መፍተሄዎች ከመፍታት አንፃር የሚኖረዉን ትርጉም እንቃኛለን። ለዚህም የፌዴራል ጥናቶች ተመራማሪና የምክክር ሂደቱ ተሳታፊ  ኃይለኢየሱስ ታዬ (ዶ/ር)እና የሐይማኖት መምህር እናየምክክር ሂደቱ ተሳታፊ ቀነዐ ለሚን እንግዳ አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  3. Sep 2

    የዓለም አቅፉ ደቡብ አዲስ ጎህ እና የብዙ ወገንተኝነት ጉዞ

    እያደገ የመጣው የብሪክስ እና የዓለም አቅፉ ደቡብ አገራት ህብረት ዓለምን ወደ እውነተኛ ሉዓላዊ፣ የጋራ እኩልነትና የብዙ ወገንተኝነት ሥርዓት ከፍ የሚያደርግ ታሪካዊ ምዕራፍ እየፈጠረ ይገኛል። “የዓለም አቅፉ ደቡብ ምዕራባውያንን እንዲሁም አሜሪካንን በእርግጥኝነት የመገዳደር ቁመና ላይ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር የዓለም አቅፉ ደቡብ ሀገራት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እያንዳንዱ ሉዓላዊ ሀገር በልኩ የሚወከልበት መድረክ እንዲሆን ይፈልጋሉ […] ብሪክስም የጸጥታው ምክር ቤት ቦታን ለመረከብ የሚያስችል የአለም አቅፉ ደቡብ ትልቅ አቅም ሆኖ ሊመጣ ይችላል” ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በዓለም አቀፍ ፖሊሲ ልማት እና ዲፕሎማሲ ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን፣ በወቅታዊ የጂኦፖሎቲካዊ ቀውሶች፣ የንግድ ጦርነቶች እና በዓለም አቀፉ ደቡብ የአጋርነት ጥረቶች ላይ ያተኩራል። በዚህ ሰፊ ረእስ ዙሪያ ለምናደርገው ውይይት ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ ያደረኝ ሲሆን፣ ቆይታችን ያደረግነውም በአዲሱ መጽሐፋቸው "ታሪፍስ ኤንድ 'ኒክሌር' ትርትስ ኦፍ ኤ ኒው ኮልድ ዎር፡ ዘ ግሎባል ሳውዝስ ክዌስት ፎር መልቲላተራሊዝም” ዙሪያ ባሉ ሀሳቦች አውድ ውስጥ ነው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

About