Continental Drift

Eden Teshome

''Continental Drift' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.

  1. 1d ago

    ንግድ፣ ውሃ እና የራስን እድል በራስ መወሰን፡ አፍሪካ የዘላቂ ልማት መሠረቶችን መገንባት ትችላለች?

    የአፍሪካ አህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና አፍሪካን አንድ የንግድ ገበያ ለማድረግ ያለመ ቢሆንም፣ ስምምነቶች ብቻ ንግድን አያሳድጉም። ንግድ እንዲያድግ የገንዘብ አቅም፣ ተስማሚ የሕግና የቁጥጥር ሥርዓት እና በአፍሪካ ገበያዎች መካከል የሚፈጠሩ የንግድ ትስስሮች ያስፈልጋሉ። “የውሃ ሉዓላዊነት ማለት መሠረተ ልማቱ፣ የገንዘብ አቅሙ እና የውሃ ሀብትን በራስ አቅም ለማስተዳደር የሚያስችል አቅም ግንባታ መኖር ማለት ነው። ማን ያቅዳል፣ ማን ይከፍላል እና ማን ይጠግናል የሚሉት ጉዳዮችም በአየር ንብረት ለውጥን ያገናዘበ፣ ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል እና ለህዝብ ተጠያቂ በሆነ መንገድ መረጋገጥ አለባቸው።” ሲሉ ከፍተኛ የውሃ ሀብት አማካሪው ወንዱ ፍሰሃ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡  በዛሬው የ ኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የአፍሪካ ነጠላ የንግድ ቀጠናን ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች ከንግድ ባለፈ በዘላቂ ልማት እና በውሃ ሉዓላዊነት ዙሪያ ያላቸውን ቁርኝት እንቃኛለን። ለዚህም የፓን አፍሪካ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ከቡር ገና እንዲሁም የሞርክ ዋተር የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ተወካይ ወንዱ ፍሰሃ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  2. 1d ago

    ሩሲያ-ቻይና ግንኙነት እና የባለብዙ ማዕከል ዓለም መፈጠር

    የሩሲያ እና የቻይና የሁለትዮሽ ግንኙነት በኢነርጂ፣ በንግድ፣ በፋይናንስ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መምጣቱ፣ ዓለም አቀፉ ሥርዓት ወደ ባለብዙ ማዕከል ሥርዓት እንዲሸጋገር እያበረከተ ይገኛል። ይህ እድገት የአፍሪካ ሀገራት ከተለያዩ አጋሮች ጋር በነፃነት እንዲሠሩ እና የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቻቸውን እንዲያስጠብቁ አዳዲስ አማራጮችን ይከፍታል። “... እንደ ቻይና፣ የሩሲያ ፌዴሬሽን እና ሌሎች ታዳጊ መካከለኛና ዓለም አቀፍ ኃይሎች በአፍሪካ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህም የአፍሪካ ሀገራት የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ካሏቸው አማራጮች መካከል እንዲመርጡ ያስችላቸዋል።” ሲሉ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡  በዛሬው የ ኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የሩሲያና የቻይና ስትራቴጂካዊ አጋርነት፣ የባለብዙ ማዕከል ዓለም መፈጠር ለአፍሪካ ያለውን ትርጉም፣ እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታቸውን ለማጠናከር ሊከተሉ የሚችሉትን አቅጣጫዎች እንቃኛለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ።

  3. 1d ago

    የቡና ንግድ እና የዕሴት መጨመር አብዮት፡ የአፍሪካ ሀብት በማን እጅ ይገባል?

    የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቶች በጥሬ ዕቃነት ከአህጉሪቱ ወጥተው፣ በሌሎች አገራት የተለያዩ ሂደቶች ተከናውነውባቸውና የተጨመረ ዕሴት ተጨምሮባቸው ለገበያ ይቀርባሉ። ይህ አካሄድ አፍሪካ ከሀብቷ ሙሉ ጥቅም እንዳታገኝ ካደረጉ ተግዳሮቶች አንዱ ነው። የዕሴት ጭማሪ አብዮት ግን አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ባሻገር ወደ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ብራንድ ግንባታና ኢንዱስትሪ ባለቤትነት እንድትሸጋገር የሚያስችል ወሳኝ አቅጣጫ ነው። "ቡናው በአብዛኛው በጥሬ ዕቃነት ይላካል፤ የዕሴት ጭማሪው ሥራ ግን ቡናው ከሚመረትበት ቦታ በጣም ርቆ በሌላ ስፍራ ይከናወናል። አብዛኛው ትርፍም የሚገኘው በዚያው ነው። በዚያም ይቀራል፤ ቡናው ወደሚመረትባቸው አገራት አይመለስም።" ሲሉ በዩጋንዳ የቡና ድርጅት ባለቤት የሆኑት ኤንድሬ ቬስትቪክ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡  በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ባሻገር የማቀነባበር፣ የብራንድ ግንባታና የኢንዱስትሪ ባለቤትነትን እንዴት ልታሳካ እንደምትችል እንቃኛለን። በዚህ ዙሪያም በዩጋንዳ የቡና ድርጅት ባለቤት ከሆኑት ከኤንድሬ ቬስትቪክ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።

  4. 1d ago

    የአፍሪካ ቀጣይ ትውልድ፡- ወጣቶችን ወደ ኢኮኖሚ ኃይል መቀየር እና ስትራቴጂካዊ አጋርነቶች

    የአፍሪካ ወጣት ሕዝብ ብዛት ለአህጉሪቱ ትልቅ የኢኮኖሚ ዕድል ቢሆንም፣ ይህ ዕድል በራሱ የሚገኝ አይደለም። በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በኢንዱስትሪ ዕድገት እና በምርት ዘርፎች ኢንቨስትመንት ሊገነባ ይገባል። "የአፍሪካ የጋራ ደኅንነት በተናጠል ጥረት ሊረጋገጥ አይችልም። ሁለተኛ፣ የአፍሪካ ስትራቴጂካዊ ደኅንነት በውጭ የገንዘብ ድጋፍ ላይ ተመርኩዞ ሊሳካ አይችልም። ሦስተኛ፣ የአፍሪካ ስትራቴጂካዊ ደኅንነት ጠንካራ የማንነት ቀውስ ባለበት ሁኔታ ሊረጋገጥ አይችልም። ስለዚህ የአፍሪካን የደኅንነት ችግሮች መፍታት የሚቻለው እነዚህን መሠረታዊ ጉዳዮች በመፍታት ነው።" ሲሉ የአፍሪካ ሪበርዝ መሥራችና ፕሬዝዳንት ኢኖክ ቱምዊን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡  በዛሬው የ ኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የአፍሪካ ወጣቶች ወደ ኢኮኖሚ ኃይል ሊቀየሩ የሚችሉበትን መንገድ እንቃኛለን። የክህሎት ሥልጠና፣ የግብርናና ኢንዱስትሪ ትስስር፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር የሚደረጉ ስትራቴጂካዊ ትብብሮች በዚህ ሂደት ያላቸውን ሚናም እንመለከታለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ።

  5. 2d ago

    ዘመናዊ ባዮቴክኖሎጂ፡ የምግብ ምርታማነት እና የገበሬዎች መብት

    "የቁጥጥር ሥርዓቱ የገበሬዎች ማኅበረሰቦችና ልዩነቶቻቸው በምርታማነት ማሳደግ ሂደት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳይደርስባቸው ማረጋገጥ አለበት። ስለዚህ ስለ ብዝኃ ሕይወት፣ ስለ መፈናቀል ወይም ስለ ገበሬዎች ዘርን ያለ ማንኛውም እንቅፋት የመሸጥ፣ የማስቀመጥ፣ የመለዋወጥ እና የመጠቀም መብት መጣስ ወይም መጥፋት ማውራት አለብን።" ሲሉ የኢትዮጵያ ዘላቂ ስርዓተ-ምግብና ስነ-ምህዳራዊ ግብርና ሕብረት ዋና ዳይሬክተር ባዩሽ ፀጋዬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡   በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ባዮቴክኖሎጂና ባዮሴፍቲ ላይ ያተኮረውን ውይይት በማስተናገድ፣ ፈጠራን ከምግብ ሉዓላዊነት ጋር ማመጣጠን ስለሚቻልበት መንገድ እንቃኛለን። ዘመናዊ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ዕድልና ተግዳሮት በመመልከት፣ የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ ከብዝኃ ሕይወት ጥበቃ፣ ከዘር ልዩነት እና ከገበሬዎች የዘር አጠቃቀም መብቶች ጋር እንዴት ሊመጣጠን እንደሚችል እንመለከታለን። ለዚህም  የኢትዮጵያ ዘላቂ ስርዓተ-ምግብና ስነ-ምህዳራዊ ግብርና ሕብረት ዋና ዳይሬክተር ባዩሽ ፀጋዬ (ዶ/ር)  እና የ'ሆምግሮውን ቪዥን' መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፀደቀ አባተ ጋር ቆይታ አድርገናል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ።

About