Drum of Changes

Zelalem Demissie

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power. Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of transformation resonating across the continent.

  1. 22h ago

    አፍሪካ እና ጊዜ፣ በማን ሰዓት ላይ ነን?

    በአፍሪካ የእጅ ሰዓት ከመግባቱ ከብዙ ዘመናት በፊት፣ ጊዜ የሚለካው በሜካኒካል ሰዓት ቁጥሮች ሳይሆን የተፈጥሮ ዑደቶችን በጠበቁ ክስተቶች ነበር። “የአፍሪካ የጊዜ አቆጣጠር ከምዕራባውያን የጊዜ ጽንሰ-ሐሳብ ፈጽሞ የተለየ ነው። ይኸውም ጊዜ በማህበራዊና ባህላዊ መነጽር የሚታይ፣ መኖርና ሊለማመዱት የሚገባ ክስተት በመሆኑ፣ ባለፈውና በአሁኑ ጊዜ ውስጥ ባሳለፍናቸው ነገሮች ላይ ትርጉም ሰጥተን እንድንገነዘበው ያስችለናል” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና እስያ ጥናቶች ማዕከል መስራች አባል ጌታቸው ካሳ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የአፍሪካን የጊዜ ጽንሰ-ሐሳብ ከዘመናዊው አለም ጋር ያለው ግንኙነት በመዳሰስ በባህላዊ እና በሰዓት ላይ በተመሰረቱ ስርአቶች መካከል ያለውን ልዩነት እንቃኛለን። ማህበራዊ አንትሮፖሎጂስት እና የአፍሪካ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና እስያ ጥናቶች ማዕከል መስራች አባል ጌታቸው ካሳ (ዶ/ር) በዛሬው ርዕሳችን ዙሪያ ሐሳባቸውን አጋርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  2. 1d ago

    ከድምፅ እስከ ታሪክ፡ የግሎባል ደቡብ ሕዝቦችን የሚያስተሳስረው የቋንቋ ገመድ

    ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ አማርኛን ማስተማር ከጀመረ 14 ዓመታት ማስቆጠሩ፣ በቻይና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የኢትዮጵያን ባህልና ቋንቋ በቀጥታ ለማስተዋወቅ ትልቅ ድልድይ ፈጥሯል። “ይህማ [ቋንቋ] በጣም ትልቅና የላቀ ሚና አለው። ቋንቋ በሁለት ሕዝቦችና በሁለት አገሮች መካከል እንደ ድልድይ የሚያገለግል ቁልፍ ጉዳይ ነው። ቻይናውያን አማርኛን ሲማሩም በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የንግድ፣ የልማትና የዲፕሎማሲ ሥራዎችን በቀጥታ ለመረዳት ያስችላቸዋል” ሲሉ በቻይና የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ መምህርትና አስተባባሪ ስንቅነሽ አጣለ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት ቋንቋ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክርበትን መንገድ ይዳስሳል። እንግዳችን በቻይና የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ መምህርትና አስተባባሪ ስንቅነሽ አጣለ (ዶ/ር) ናቸው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  3. 1d ago

    ከአፍሪካ ወሰን ባሻገር፡ የስደት ፖሊሲዎችን ማን፣ ለምን ይቀርጻል?

    የአውሮፓ ሀገራት የስደት እና የድንበር ፖሊሲ ድንበራቸውን በራሳቸው አካባቢ ብቻ የሚገድብ ሳይሆን፣ ስደትን ከመነሻው እና ከመሸጋገሪያ ሀገራት ጀምሮ ሄዶ መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ነው። “አውሮፓ ሀገራት የውጪ ድንበራቸውን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት የስደት ቁጥጥር ፖሊሲያቸው በአፍሪካ መነሻ እና መሸጋገሪያ ሀገራት ውስጥ ዘልቆ በመግባት ስደትን ከምንጩ ለመቆጣጠር ላይ ያተኮረ ነው [...] አውሮፓውያን በስደት ቁጥጥር ሰበብም የአፍሪካውያን ፖሊሲዎች [የፍልሰት] ቀረፃ ሂደት ላይ ጫና ያሳድራሉ” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ሜሮን ዘለቅ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት፤ በአፍሪካ እና በአውሮፓ መካከል ስላለው የስደት አስተዳደር፣ አህጉራዊ አቅጣጫዎች፣ የሉዓላዊነት ተግዳሮቶች፣ እንዲሁም የሰለጠነ ሰውኃይል ፍልሰት ላይ ሰፊ ዳሰሳ እናደርጋለን። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ሜሮን ዘለቀ (ዶ/ር) ደግሞ እንግዳችን ናቸው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአማርኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  4. 1d ago

    የብሪክስ ንግድ፦ አዳዲስ ዕድሎች፣ አዳዲስ ገበያዎች

    የብሪክስ አባል አገራት እርስ በርሳቸው የሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ መጠን ከሃያ ዓመታት በፊት ከነበረበት 84.2 ቢሊዮን ዶላር በብዙ እጥፍ አድጎ 1.17 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ደርሷል። “የብሪክስ ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ የዶላር ጥገኝነትን በመቀነስ ዓለምን ወደ ባለብዙ ዋልታ ኢኮኖሚ እያሸጋገረ ነው [...] ኢትዮጵያም አባል መሆኗ [የብሪክስ] የንግድ ማዕቀፎችን ለማብዛት፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና ቴክኖሎጂ ለማግኘት ትልቅ ዕድል ይፈጥርላታል” ሲሉ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ማኔጅመንት የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ ዱጋሳ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ የ2026 የብሪክስ ንግድ ዘገባ ላይ ዳሰሳ በማድረግ፣ የብሪክስ መስፋፋት ለኢትዮጵያ የወጪ ንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት የሚፈጥራቸውን ዕድሎች በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ማኔጅመንት የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ ዱጋሳ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ጋር ይቃኛል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  5. 1d ago

    የነጻነት ዋጋ – የሃይቲ ያልታየው ገፅ

    የመጀመሪያዋ ነፃ የጥቁር ሪፐብሊክ የሆነችው ሃይቲ ዛሬ ላለችበት ውጥንቅጥ ምክንያት የጥቁር ህዝብ ድክመት ሳይሆን፣ የሁለት ክፍለ ዘመናት የምዕራባውያን የሀብት ዘረፋ እና የጣልቃ ገብነት ሴራ ውጤት ነው። “የሄይቲ ወቅታዊ ችግሮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሀገሪቱ የመጀመሪያ ስቴት ምስረታ ጀምሮ የጀመሩ ናቸው፤ አሜሪካውያንም ሄይቲን የጥቁር ነፃነት ፊት አውራሪ በመሆኗ እና ይህ አስተሳሰብ ወደ ሰሜን አሜሪካ ሊዛመት ይችላል በሚል ስጋት ይመለከቷታል” ሲሉ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቱዩት የባለብዙ ወገን መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጉዳዮች ተመራማሪ አዲስ አለማሁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ያልተነገረውን የሃይቲ የጀግንነት ታሪክ እና የምዕራባውያን ታሪካዊ በደሎች ሀገሪቱን ላለችበት ውጥንቅጥ እንዴት እንደዳረጓት በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቱዩት የባለብዙ ወገን መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጉዳዮች ተመራማሪ አዲስ አለማሁ ጋር ዳሰሳ አድርጓል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

About

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power. Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of transformation resonating across the continent.