Sovereignty Sources

ዐቢይ ሀብታሙ

ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች  ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

  1. EPISODE 2

    የአፍሪካ የዲጂታል ሉዓላዊነት መንገድ ፣ ሾልከው የሚወጡ መረጃዎችን መቀነስ እና የአካባቢ መሠረተ ልማት ግንባታ

    የሶቨርኒቲ ሶርስ የዕለቱ ዝግጅት ትኩረቱን በሳይበር ደህነነትን ላይ ሲያደርግ ፣ የአፍሪካ ሀገራት ለዜጎቻቸው የሚሰጧቸዉን  ዲጂታል አግልግሎቶችና  የተደቀነባቸውን የሳይበር ጥቃቶች በስፋት ይዳስሳል፡፡ ለዚህም ከፍተኛ የሶፍትዌር ኢንጅነር እና የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት አበልፃጊ /ዴቨሎፐር/  አቤል በነበሩን  ጋብዘናል፡፡ በአፍሪካ እያደገ የመጣው ዲጂታላይዝ የሆነ አገልግሎት አሰጣጥ ምክንያት በማድረግ የአፍሪካ ሀገራት የሳይበር ደህንነትን በተመለከተ ንቁ የሆነ አካሄድ መከተል ይገባቸዋል፡፡ ““ለምሳሌ አሁን ላይ የምንጠቀመው የመረጃ ማዕከል ሊሆን ይችላል፣ ኔትዎርክ ኢንተርኔት ኤክስቼንጅ ፖይንቶቻችንም ሊሆኑ ይችላሉ እንዳሉ ከምዕራባውያን ጋር የተገናኙ ነገሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ ለእነዚህ ነገሮች መፍትሄ መስጠት፣ ለምሳሌ አፍሪካውያን እንደ አፍሪካ ተቀናጅተው አንድ ኢንተርኔት ኤክስቼንጅ ፖይንት እንዲኖራቸው ሁለተኛ የራሳቸው የመረጃ ማዕከል ቢኖራቸው  መረጃ የመውጣቱ ዕድል ይቀንሳል፡፡" ሲል ከፍተኛ የሶፍትዌር ኢንጂነር እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት አበልፃጊ ወይም ' ዲቨሎፐር' አቤል በነበሩ ተናግሯል ።   ይህም  ከፖርታል ሳይበር ጥቃት  ሚስጥራዊ  መረጃን ፣ ዲጂታል መሠረተ ልማትን እና አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶችን  መጠበቅ ላይ ሚናው ወሳኝ ነው ፣ ለዚህ ደግሞ ዲጂታል ሉዓላዊነት ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ‘‘ ዲጂታል ሉዓላዊነት - አንድ ሉዓላዊ የሆነ ተቋም የራሱን ፣ ስትራቴጂካዊ መረጃዎችን ወይም ሐብቶችን መጠበቅ እንድትችል ይረዳሃል [....] ይህ ደግሞ የራስን የዲጂታል መሰረተ ልማት መገንባትህ ስለማይቀር ለሀገር ውስጥ ስራ ፈጠራዎችም  እድል ይሰጣል’’ ብሏል - ከፍተኛ የሶፍትዌር ኢንጅነር እና የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት አበልፃጊዉ  አቤል በነበሩ ፡፡ ይህም በመረጃ ሉዓላዊነት ላይ አዎንታዊ ሚናን እንደሚጫወት ባለሙያው ተናግረዋል ፡፡ የሳይበር ጥቃት አይነቶች እንዴት ያሉ ናቸዉ ?  በታዳጊ ሀገራት ያሉ  አገልግሎት ሰጪዎች  የሳይበር ጥቃት የሚያጋልጡ ክፍትቶቻቸዉ ምንድን ናቸው ? ለጥያቄዎቹ መልስ የሚሆኑ እና ሌሎች ሐሳቦችን በሶቨርኒቲ ሶርስስ ላይ ይከታተላሉ።

    1 hr
  2. EPISODE 3

    ሠው ሰራሽ አስተውህሎት፡የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት አዲሱ ዘመን በኢትዮጵያ

    ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፉ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ የብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲዋን በማሻሻል እየሰራች ነው ። ለዚህም ከሩሲያ ጋር ትብብርን በመፍጠር ማርሽ ቀያሪ  አጋርነትን መሥርታለች። ትብብሩ ከሮቦቲክስ እስከ ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ድረስ በደቡባዊው ዓለም ውስጥ ፈጠራን እንደ አዲስ  ያስተዋውቃል። የሶቨርኒቲ ሶርስስ ዝግጅታችንም በጉዳዩ ላይ  የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ  ባህሩ አባስን ወደ ስፑትኒክ ስቱዲዮ ጋብዞታል ። የባለሙያው ዕይታ፡ “ይህ የቴክኖሎጂ ጉዳይ ብቻ አይደለም -  የሉዓላዊነት ጉዳይም እንጂ። ኢትዮጵያ የሠው ሰራሽ አስተውሎት አቅሞቿን ወደ ላቀ ደረጃ ማስፈንጠር ትችላለች፣ ሩሲያም በአፍሪካ የዲጂታል ምጣኔ ሐብት ላይ ያላትን ተሳትፎ ታረጋግጣለች” ሲል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያው  ባህሩ አባስ ተናግሯል። ከጂኦ ፖለቲካ ባሻገር፡ በኢትዮጵያ በሠው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ማዕቀፍ ፣ የሩሲያ  እና  ብሪክስ አባል ሀገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን  መሠረት ያደረገ አጋርነት የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ ተራማጅ ዘርፍ እንዲገነቡ ያነሳሳቸዋል። 🎙በሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕርግራም የሚቀርበውን ሙሉ መሠናዶ ለመከታተል ዝግጁ ነዎት?

    1 hr
  3. EPISODE 4

    ከፍታን የሚያልመው የአፍሪካ አቭዬሽን

    በአፍሪካ ሰማይ መልካም ዕድሎች ያንዣብባሉ! የአቪዬሽን ዘርፉ ለጠንካራ እድገት ተሰናድቷል፣ በዚህም ለአየር መንገዶች፣ ባለሃብቶች እና አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ ዕድል ፈጥሯል። ነገር ግን ይህን ከፍታ የሚያነሳሳው ምንድነው - ደግሞስ ምን ወደኃላ ሊጎትተው ይችላል? በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ መሠናዶ በጥልቀት ለመወያየት የአቪዬሽን ዘርፍ ባለሙያው ዮናታን መንክር በእንግድነት ጋብዘናል። የአቪዬሽን ዘርፉ ምን ያህል ሁነኛ መሣሪያ ስለመሆኑ ባለሙያው ዮናታን ሲያብራሩ፡-   “አቪዬሽን ወይም የአየር ትራንስፖርት የሚሰጠው ነገር የመንገደኞችን ሰዓት መቀነስ ነው። ይህ ዕውን የሚሆነው የአየር ትራንስፖርት ለንግድ  አገልግሎት  ተደርጎ ሲወሰድ ነው። ነገር ግን አቪየሽኑን በአጠቃላይ ከወሰድን፣ ብዙ ነገሮችን ማንሳት እንችላለን፣ የህክምና ቱሪዝም ፣ የግብርና አቪዬሽን ፣ በዋነኛነት  ለቱሪዝም ተግባራት ፣ ለአየር ካርታ ስራ እና ለምትለው ስራ ሁሉ አጠቃላይ የአቪዬሸን ዘርፉ ትልቅ ጥቅም ነው ያለው''  ብለዋል ። ዮናታን ዘርፉ በአህጉሪቱ እንዳይጎለብት ስለሚያደርጉት ማነቆዎች በተመለከተ ሲያስረዱ ፦ “የአፍሪካ አቪዬሽን ዘርፍ ዕድገት ማነቆ ከሆኑ ነገሮች መካከል መሠረ ልማት አንዱ ነው። መሰረተ ልማት ሲባል የረጅም ጊዜ ትስስር ነው። ይህ የአውሮፕላን ማረፊያ ወይም በዙሪያው የሚኖሩ ፋሲሊቲዎችን መገንባት ማለት አይደለም። ስለዚህ መንገዶች እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው።ይህም ከአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል የሚያልፍ መንገደኛ የሚጓዝበት ነው ''  ሲሉ ተናግረዋል በአፍሪካ በዘርፉ ያሉ ትብብሮችም ፣  ከኢትዮጵያ ጠቃሚ ልምዶች የሚቀሰምባቸው ቢሆኑ አዋጭ ስለመሆኑ የአቪዬሽን ባለሙያው ዮናታን መንክር  ተናግረዋል። “አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የጎለበተ የሠው ኃይልና ቴክኖሎጂ እንዲኖራቸው በአፍሪካ ቀዳሚ ወደሆነው  የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጠጋታቸው ጥሩ ማሳያ ነው። ነገር ግን ይህ የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የብዙዎች ነው መሆን ያለበት። ስለዚህ ሀገራት በቴክኖሎጂ፣ በምጣኔ ሐብትና በሰው ኃይል አጋርነት ላይ እንዲተባበሩ ፍላጎት ሊኖር ይገባል።  እነዚህ ነገሮች ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪ እድገት እና ልማት በጣም ቁልፍ ናቸው” ብለዋል። ስለ አቪዬሽን ዘርፉ የበለጠ ለመረዳት በስፑትኒክ አፍሪካ ተሰናድቶ የሚቀርበውን ይህን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተሰናዳውን የሶቨርኒቲ ሶርስስ መሠናዶ ይከታተሉ ።

    1 hr
  4. EPISODE 5

    የአፍሪካ የክትባት ነፃነት: ወደ ግብ የሚያደርስ ህልም?

    ፍሪካ ከምትጠቀመው ክትባት በራሷ የምታመርተው 1% ብቻ መሆኑን ያውቃሉ? የአህጉሪቱ የጤና ደህንነት መሠረት ያደረገው የውጭ ድጋፍ ላይ እንደመሆኑ እርምጃ የመውሰጃ ጊዜው አሁን ነው! የሶቨርኒቲሶርስ ፕሮግራም በዛሬው መሠናዶው በክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች ሀሳባቸውን እንዲያጋሩን በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጨቅላ ህፃናት ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ጡረኝ ስዩም ን ጋብዟቸዋል። ዶ/ር ጡረኝ ሀገር በቀል ክትባት ማምረት የሚያስፈልግበት ምክንያትን ሲያስረዱ፡ “ክትባት በብዙ መጠን ማምረት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ምክንያቱም አቅርቦት አለመኖር ከማነቆዎች መካከል አንዱ ስለሆነ። ስለዚህ፣ በራሳችን አውድ የክትባት ምርት ሊኖረን ይችላል ነገር ግን ብዙ ሥራዎች ፣ ኢንቨስትመንት እና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ነው። ” ሲሉ ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራት በጋራ ተጣምረው ክትባት ማምረት ስለሚችሉባቸው መንገዶች  ዶ/ር ጡረኝ ሲያብራሩ :- “የአፍሪካ ሀገራት አንድ ላይ በመሆን ይህን ችግር መፍታት እንችላለን። ነገር ግን ምንም እንኳ አንድነት ብንፈጥርም፣ በቁርጠኝነት  የረጅም ጊዜ የጋራ መግባባት የሚፈልግ ጉዳይ ነው። እናም እንደጠቀስኩት ለክትባት ምርትና ልማት ብዙ መመዘኛዎች አሉ።  ስለዚህ ግቦቹን ለማሳካት እነዚያ ሁሉ መመዘኛዎቾ ሊታቀዱና ሊሰሩ ይገባል።'' ብለዋል። ➡️ የጅምላ ምርት - እጥረትን ለመቅረፍ ➡️ የፓን አፍሪካ ትብብር - ለረጅም ዘመን ስኬት ➡️ ኢንቨስትመንትና ቁርጠኝነት - ራዕይን ወደ እውነታነት ለመለወጥ ስለሀገር በቀል ክትባት ምርት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የበለጠ ለመረዳት ፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበዉን ፣ የሶቨርኒቲ ሶርስስ  ሙሉ ፕርግራምን ይከታተሉ።  ሙሉ ፕርሮግራሙን ለማድመጥ ዝግጁ ነዎት?

    1 hr

About

ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች  ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣