Turning Africa Forward

በርናባስ ተስፋዬ

Turning Africa Forward - ከቴክኖሎጂ እና አስተዳደር እስከ ባህል፣ ዲፕሎማሲ እና ከዚያም ባለፈ፤ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ላቀ ደረጃ ለማደግ የምታደርገውን ጽኑ ጉዞ የሚመሩ ምልከታዎችን በዝርዝር እንዳስሳለን።

  1. Aug 12

    የሳህል ሀገራት አዲስ ስትራቴጂ፡ የ2032 አፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ ጥያቄ እና የቀጣናው አዲሱ የትብብር ምዕራፍ

    « በሁሉም መስፈርቶች—በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በጂኦ-ስትራቴጂ—ይህ የጨረታ ጥያቄ ታላቅ የዲፕሎማሲ ስኬት ነው። ውድድሩን ማስተናገድ የታገደ/የተገለለ የሚለውን አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ ያስቀራል፣ ያከሽፋልም። [...] እስካሁን ተጽእኖ ፈጥሮ የቆየው የታሪክ አቀራረብ ይህንን ቀጠና በግጭት ብቻ አሳንሶ አሳይቶታል። ይህ የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት ጥያቄ የምድር ላይ እውነታውን ያጋልጣል—ቀጠናው ለዓለም አቀፍ አጋርነት ክፍት እና ብቁ መሆኑን ያሳያል፡፡» ሲሉ የከፍተኛ ህዝብ ጉዳዮች ተንታኝ የፓን-አፍሪካኒዝም እና የልማት ስፔሻሊስት ኦሉሶጂ አጃኦ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በመጀመሪያው ክፍል የሳህል ሀገራት ህብረት  የተጣለባቸውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጫናዎች በመቃወም፣ ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖአቸውን ለማሳደግ እና ቀጣናዊ መሰረተ-ልማቶችን ለማፋጠን ያቀረቡትን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን በ2032 በጋራ የማስተናገድ ጥያቄ እና የስፖርት ዲፕሎማሲ ፋይዳን ከፓን-አፍሪካኒስት እና የልማት ስፔሻሊስቱ ኦሉሶጂ አጃኦ ጋር በጥልቀት እንወያያለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፤ የኢትዮጵያን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤን ማዕከል በማድረግ፣ ከውጭ የሚገቡ የህግ ማዕቀፎች ያሉባቸውን ጉድለቶች በመዳሰስ እና እንደ ሽምግልና እና ገዳ ያሉ ባህላዊ የእርቅ መድረኮችን በማዘመን ዘላቂ ሰላምን እና ሀገራዊ ሉዓላዊነትን የመገንባት ሂደትን ከህግ እና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ፡

  2. Aug 11

    የአፍሪካ የኃይል ሉዓላዊነት፣ የቀጠናው መሠረተ ልማት ትስስርና የውጭ ዕዳ ዑደትን የመስበር ታሪካዊ ትግል

    ''አፍሪካ ወደ ብልጽግና የምታደርገው ጉዞ መሠረት ሊኖረው የሚገባው በራስ አቅም በሚደገፉ መሠረተ ልማቶችና የውጭ ዕዳ ወጥመዶችን በቆራጥነት ባለመቀበል ላይ ነው ። እውነተኛ ነፃነት ማለት ድፍድፍ ዘይትን ወደ ጨርቃጨርቅ፣ መድኃኒቶችና ማዳበሪያዎች መለወጥ የሚያስችሉ የተቀናጁና የተራቀቁ የፋብሪካ መዋቅሮችን በራስ ባለቤትነት ማስተዳደር መቻል ነው '' ሲሉ የዓለም አቀፉ የንግድ ምክር ቤት (ICC) ምክትል ሊቀመንበር ኢንጂነር ፓትሪክ ኦባዝ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል ።   በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራም፤ በምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (EAC) ዘንድ እንደ ታሪክ ቀያሪ የተቆጠረውና ከ25 እስከ 30 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተውን የታንጋ የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት የፋይናንስ፣ የፖለቲካና የቴክኒካዊ መዋቅር በጥልቀት እንፈትሻለን ። ነዳጅን ለመገበያየት የምስራቅ አፍሪካ የጋራ ገንዘብን በማምጣት የአሜሪካ ዶላር ጥገኝነትን ለማስቀረትና ለአነስተኛና መካከለኛ አንቀሳቃሾች (SMEs) ምን ዓይነት መዋቅራዊ ዕድሎችን ይዞ ይመጣል? ስንል ከዓለም አቀፉ የንግድ ምክር ቤት (ICC) ምክትል ሊቀመንበር ከኢንጂነር ፓትሪክ ኦባዝ ጋር ሰፊና ጥልቅ ቆይታን አድርገናል። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  3. Aug 8

    የአፍሪካ ቋንቋዎችና 'ኤአይ'፦ ከምዕራባውያን የበላይነት ወደ ዲጂታል ሉአላዊነት

    ''የአፍሪካ ቋንቋዎችን በዲጂታል አካታች ማድረግ የሚቻለው የምዕራባውያንን የቋንቋ ሞዴሎች በአፍሪካ እውነታዎች ላይ በግድ በመጫን አይደለም፤ የዲጂታል ስርዓቶች የጾታ አገላለጽን ሲያዛቡ ወይም አካባቢያዊ የአነጋገር ዘይቤዎችን ሲስቱ፣ ይህ ተነጥሎ የሚታይ የቴክኒክ ችግር ሳይሆን የአፍሪካን ሰዋሰዋዊ መዋቅሮች በዝምታ የሚያጠፉ፣ የአፍሪካን እውነታ የማያንጸባርቁና በምዕራባውያን ማዕከልነት የተቃኙ የመረጃ ቋቶች ውጤት ነው'' ሲሉ በምስራቅ አፍሪካ የሂሳብ ሳይንስ ምርምርና ኢኖቬሽን ማዕከል የኤአይ እና ኤንኤልፒ ተመራማሪው ዶ/ር ዋለልኝ ተዋበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል። በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በመጀመሪያው ክፍል ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የቋንቋ ማቀናበሪያ ቴክኖሎጂዎች ከአፍሪካ ቋንቋዎች ህልውና ጋር ያላቸውን ቁርኝት፣ ከኤአይ እና ኤንኤልፒ ተመራማሪው ዶ/ር ዋሌልኝ ተዋበ ጋር በጥልቀት እንወያያለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፤ ወደ አለም አቀፉ የኤአይ ሉዓላዊነትና የብዙ-ዋልታ ስርዓት በመሸጋገር፤ በሻንጋይ የተመሰረተው የአለም አቀፍ ኤአይ ትብብር ድርጅት ለአፍሪካና ለታዳጊ ሀገራት የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የውድድር አቅም እና የዲጂታል ሉዓላዊነት መከበር ያለውን ፋይዳ ከኤአይ አስተዳደርና እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂካዊ አማካሪው ቱሁ ኑግራሃ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

  4. Aug 8

    የአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ግብረ-ኃይል አፋጣኝ ተግበራዊነት እና የአረንጓዴው ንቅናቄ ኢኮኖሚያዊ እውነታዎች

    ''የአፍሪካ የጋራ ሰላምና ደህንነት ራዕይ እውን ሊሆን የሚችለው የአህጉሪቱን ችግሮች በአፍሪካውያን እቅድና አቅም መፍታት ስንችል ነው፤ አፍሪካ የሚያጋጥሟትን በርካታና ወሰን ተሻጋሪ የደህንነት ስጋቶች ሀገራት በብቸኝነት መወጣት አይችሉም። ስለዚህ የአፍሪካ ተጠባባቂ ኃይልን (Africa Standby Force) ከተቋማዊ ማዕቀፍነት ወደ ተግባራዊ የመከላከል አቅም ማሸጋገርና የራሳችንን የፋይናንስና የቴክኒክ አቅም መገንባት ከወታደራዊ ጣልቃገብነትና ጥገኝነት ለመላቀቅ ወሳኝ እርምጃ ነው'' ሲሉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ የስርዓተ-ትምህርት ልማት ምክትል አዛዥ ደምሌ ሞላው(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል። በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በመጀመሪያው ክፍል የኢትዮጵያን አህጉራዊ ጥሪ መነሻ በማድረግ የአፍሪካን ተጠባባቂ ኃይል በአፋጣኝ ወደ ሥራ ማስገባት፣ በአፍሪካ ቀንድና በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ያለው አስፈላጊነት፣ የውጭ ጣልቃገብነትን የመቀነስ አቅምና ከአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ጋር ያለውን ቁርኝት ከመከላከያ ኮሌጅ የስርዓተ-ትምህርት ልማት ምክትል አዛዥ ደምሌ ሞላው(ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንወያያለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፤ ወደ አህጉራዊ ኢኮኖሚና የአየር ንብረት ለውጥ እውነታዎች በመሸጋገር፤ የአረንጓዴው ንቅናቄ ከውጭ የፖሊሲ ጫናዎች ተላቆ ኢኮኖሚያዊ አቅምን፣ የኃይል አቅርቦት እጥረትንና የካፒታል ፍሰት እውነታዎችን ያገናዘበ ማድረግ ስለሚያስፈልግበት ሁኔታ፤ ከቀድሞው የኢንቨስትመንት ባንከርና የኢኮኖሚክስ ባለሙያ ቮይቴክ ቦጉትስኪ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ ፡

  5. Aug 8

    የሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ለመዋቅራዊ የፋይናንስ ሉዓላዊነት

    ''የግሎባል ሳውዝ ሀገራት የምዕራባውያንን የክፍያ ሥርዓቶች አልፈው አማራጭ መዋቅር ለመዘርጋት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተቃርበዋል፤ ይህም አሁን ላይ ከፖለቲካዊ መፈክር ባለፈ በተግባር የደህንነት ማረጋገጫ ዘዴ ሆኗል'' ሲሉ የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ከፈለኝ ኃይሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ የዶላርን የበላይነት እና የምዕራባውያንን የእዳ ወጥመድ በመጋፈጥ፣ የሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም (SPIEF) ለአፍሪካ ሀገራት ምን ዓይነት አስተማማኝ የፋይናንስ አማራጮችን ይዞ ይመጣል? በሀገር ውስጥ ገንዘብ የመገበያየት እና የንብረት ልውውጥ (Barter Trade) ሥርዓቶችስ የአህጉሪቱን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ ያላቸው ሚና ምንድነው? ስንል ከቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ከፈለኝ ኃይሉ ጋር ሰፊ ቆይታን አድርገናል። በክፍል ሁለት ደግሞ፣ የአህጉሪቱን የህዝብ ጤና፣ የእንስሳት ሀብትና የአካባቢ ጥበቃን በተቀናጀ መልኩ ለመታደግ የወጣው አዲሱ የጸረ-ተህዋስያን ቁጥጥር መመሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የ"ዋን ሄልዝ" ስትራቴጂ በማገዝ ረገድ ስላለው ሚና በጥልቀት እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

  6. Aug 4

    የሕዋ ቴክኖሎጂ፣ የትምህርት እና የባህል ሉዓላዊነት፡ የአፍሪካ አዲሱ የዕድገት ምዕራፍ

    ''የሕዋ ቴክኖሎጂ ልማት ለአፍሪካ ሀገራት የቅንጦት ፍላጎት ሳይሆን፣ የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ እና የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል በመሠረታዊነት አስፈላጊ ነው፤ ይህንንም እውን ለማድረግ በእስያ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የጋራ ትብብር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማጠናከር ወሳኝ ነው፡፡'' ሲሉ የእስያ-አፍሪካ የንግድ ትስስር አማካሪ ጉንተር ባይሰል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ በመጀመሪያው ክፍል እ.ኤ.አ ኦገስት 10-11/2026 የሚካሄደውን የ'አፍሪካ ዓለም አቀፍ የሕዋ ጉባኤ' (ISSA) መነሻ በማድረግ፤ የአፍሪካ የሕዋ ቴክኖሎጂ እና የሳተላይት መረጃዎችን ለሀገራት የኢኮኖሚ እድገት እና ለዲጂታል ሉዓላዊነት የመጠቀም ወሳኝ አቅምን በጥልቀት ዳስሰናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የትምህርት ሥርዓታችንን ከውጭ ጥገኝነት በማላቀቅ የሀገር በቀል እውቀቶችን ማዕከል ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ፣ እንዲሁም የራሳችንን የፋይናንስ ሥርዓት እና የብድር ደረጃ መመዘኛ ተቋማት በመገንባት ኢኮኖሚያዊ ነፃነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት መንገድ ላይ ከዘርፉ ከፍተኛ ምሁራን ጋር በሰፊው ተወያይተናል። በመጨረሻው ክፍል ደግሞ የአፍሪካን ጥበብ፣ ፊልም እና የፈጠራ ስራዎች የጂኦ-ፖለቲካዊ እና የዲፕሎማሲ አቅም በማድረግ፣ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ጥላ ስር ከአለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር እኩል የመደራደር ስልታዊ መንገዶችን በስፋት ተመልክተናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ ፡

  7. Jul 25

    የጂኦፖለቲካዊ ሽግግሮች እና የአገር በቀል አረንጓዴ ቴክኖሎጂ መዋቅራዊ ሉዓላዊነት

    ''የዩክሬን ቀውስ በአንድ ጀምበር የተከሰተ ሳይሆን ምዕራባውያን የአንድዮሽ የበላይነታቸውን ለማስቀጠል እና ዓለም ወደ ብዙሃን የኃይል ማዕከል እንዳትቀየር የጠነሰሱት የረጅም ጊዜ የውክልና ጦርነት ውጤት ነው'' ሲሉ የህግ ባለሙያው አቶ ዳንኤል ፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በምዕራባውያን የሚመራው ኔቶ እና የአውሮፓ ህብረት ከ2014ቱ የኪየቭ መፈንቅለ መንግስት ጀምሮ ግጭቱን እንዴት እንደጠነሰሱት፣ እንዲሁም የሰላም ስምምነቶችን (Minsk Agreements) የፈረሙት ለሰላም ሳይሆን ዩክሬንን በሩሲያ ላይ እንደ ተተኪ ጦረኛ (Proxy) ለማደራጀትና ጊዜ ለመግዛት እንደነበረ ምዕራባውያን ልሂቃን ራሳቸው ያመኑበትን እውነታ የጂኦፖለቲካ እና የህግ እይታዎችን መነሻ በማድረግ ከህግ ባለሙያ አቶ ዳንኤል ፍቃዱ ጋር ጥልቅ ትንተና አድርገናል። በክፍል ሁለት ደግሞ፣ አፍሪካ የሌሎችን እርዳታ ሳትጠብቅ በራሷ የግብርና ሃብትና በአገር በቀል ኢንጂነሪንግ እውቀት ራሷን ወደ ላቀ ምዕራፍ የምታሸጋግርበትን ታሪካዊ የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ አብዮት እንቃኛለን። የኢትዮጵያው "አገልግል ኢኮ-ፓኬጂንግ" የግብርና ተረፈ ምርቶችን በአገር ውስጥ ማሽነሪዎች በመቀየር ርካሽ ፕላስቲኮችን እንዴት እየተካ ይገኛል? እንደ ብሪክስ ሴቶች ቢዝነስ አሊያንስ ያሉ የደቡብ-ደቡብ ጥምረቶችን በመጠቀምስ አገር በቀል የቴክኖሎጂ ፈጠራን ወደ ህንድ እና ደቡብ አፍሪካ ለማሻጋር ምን ዓይነት ስልታዊ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው? በሚሉት አበረታች ነጥቦች ዙሪያ ከተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ተባባሪ መስራች አፎሚያ አንዱአለም ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።   ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

About

Turning Africa Forward - ከቴክኖሎጂ እና አስተዳደር እስከ ባህል፣ ዲፕሎማሲ እና ከዚያም ባለፈ፤ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ላቀ ደረጃ ለማደግ የምታደርገውን ጽኑ ጉዞ የሚመሩ ምልከታዎችን በዝርዝር እንዳስሳለን።