ማሕደረ ዜና

ማሕደረ ዜና፣ ዓለም መሪዎች እየተግባቡ ይሆን ወይስ ግራ እያጋቡ

ሰዉዬዉ ከመቸኮላቸዉ የተነሰ በእስራኤል ላይ የሚለዉን በኢራን ላይ የተቃጣ አደጋ ብለዉት ነበር።ቸኩለዉ አሉት።ፈጥነዉ አረሙት።ኔታንያሁ እስራኤል ከመጥፋት አደጋ፣ ዓለምም ከመገደል ሥጋት ድኗል ቢሉም የለንድን፣ የፓሪስና የበርሊን መሪዎች አልተቀበሉትም። እንደ አሜሪካ ሁሉ የእስራኤል የቅርብ ወዳጆች፣ የኢራን ጠላቶች ፈረንሳይ፣ ብሪታንያና ጀርመን የኢራን የኑክሌር መርሐ-ግብር ያሰደረዉ ሥጋት አልተወገደም ይላሉ።ወይም የኔታንያሁን ማረጋገጪያ አላመኑትም።በሶስቱ ሐገራት ግፊት የተሰየመዉ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በኢራን ላይ ዳግም ዓለም አቀፍ ማዕቀብ እንዲጣል ወስኗል።